ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ታሪክ ታላላቅ እና አይቻሉም የተባሉ ጉዳዮችን እውን ያደረግንበት የስኬት ዓመት ነበር ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም የሀገሪቱን ግብርና መር የኢኮኖሚ አካሄድ፤ ከአንድ ዘርፍ ወደ ብዝኃ ዘርፍ በመቀየር ተጨባጭ ለውጥ እየመጣ ነው ብለዋል።
በዚህም 5 ዋና ዋና ዘርፎች ተለይተው ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም እና ቴክኖሎጂ ላይ በመስራት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።
መንግሥት የኢትዮጵያን ልማት ለማፋጠንም ከግሉ ዘርፍ ጋር በጥምረት፤ ከሕዝብ እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር ተጣምሮ የተፋጠነ ዕድገት እውን ለማድረግ እየተጋ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በአረንጓዴ አሻራ 48 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ጠቅሰው በዓለም ትልቁ የደን ማልማት ሥራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በሰለሞን ከበደ