Search

ኢትዮጵያውያን ሲተባበሩ ተአምር እንደሚሠሩ ዛሬ ዳግም ታይቷል። - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

"በመትከል ማንሠራራት" በሚል መሪ ቃል ፣ በአንድ ቀን 700 ሚልዮን ዛፎችን ለመትከል ያቀድነው ዕቅድ ከታሰበው በላይ ተሳክቷል።
አመራሮችና ሠራተኞች፣ የግልና የመንግሥት ተቋማት፣ ኤምባሲዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ሕጻናት፣ ወጣቶች፣ ጎልማሶች፣ አረጋውያን፣ ወንዶችና ሴቶች ለአረንጓዴ ዐሻራ፣ ዛሬ በማለዳ፣ ከወፎች ቀድመው ወጥተዋል።
አረንጓዴ ዐሻራ የኢትዮጵያውያን ባህል እየሆነ ነው። የኢትዮጵያን መልክም እየቀየረ ነው። የኢትዮጵያን ታሪክም እየቀየረ ነው። የዓለምንም መልክ እየቀየረ ነው።
ይሄንን ተልዕኮ የሚያስተባብሩትን፣ ጥሪያችንን ሰምተው ወጥተው የተከሉትን ሁሉ እናመሰግናለን። ኢትዮጵያውያን ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ዜጎች በብዛት እና በምልዐት ስላደረጉት ተሳትፎ በኢትዮጵያ ስም እናመሰግናለን።
መትከል ለልጆቻችን ጥላ መዘርጋት ነው!