Search

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የቻይና የአፍሪካ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛን ተቀብለው አነጋገሩ

ረቡዕ ጥቅምት 25, 2019 42

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የቻይና የአፍሪካ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ሊዩ ሺያንፋን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በአፍሪካ ሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ ለልዩ መልዕክተኛው ገለጻ ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የቻይና የአፍሪካ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ሊዩ ሺያንፋ በበኩላቸው፣ ሀገራቸው በአፍሪካ ሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ ገንቢ ሚና ለመጫወት ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: