Search

ኢትዮጵያ ከካዛኪስታን ጋር በንግድ እና ኢንቨስትመንት መስኮች ለመሥራት ዝግጁ ናት፡- አፈ ጉባኤ አህመድ ሽዴ

ረቡዕ ጥቅምት 25, 2019 44

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አህመድ ሽዴ በኢትዮጵያ ከካዛኪስታን አምባሳደር ዣላጋስ አዲልባየቭ ጋር የሁለቱን ሀገራት የፓርላማና የኢኮኖሚ ትብብር ለማጠናከር ተወያይተዋል።

አፈ ጉባኤው በዚሁ ወቅት፣ ኢትዮጵያ ከካዛኪስታን ጋር በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በሌሎች መስኮች ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ገልጸው፣ ትብብሩን ለማጎልበት ሁለቱ ሀገራት በቅርበት እንደሚሠሩ አስረድተዋል።

አምባሳደሩ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በተለያዩ መስኮች እየተጠናከረ መምጣቱን ጠቅሰው፣ በሀገራቱ መሪዎች በተደረሱ የትብብር ስምምነቶች ላይ በመመሥረት የልምድ ልውውጡን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።

የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ ባለፈው ዓመት ከ61 በመቶ በላይ ማደጉን ጠቅሰው፣ የንግድ ግንኙነቱን ይበልጥ ለማሳደግ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ማስፋትና ከእርስ በርስ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተሞክሮ መማማር እንደሚገባቸው አመላክተዋል።

በውይይቱ የሁለትዮሽ የፓርላማ ቡድኖችን ማቋቋምና ማጠናከር እንዲሁም የሁለቱ ፓርላማዎች ባለሙያዎች ልምድ እንዲለዋወጡ ማድረግ እንደሚገባ ተነስቷል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: