ብዝሃ ዘርፍ ትብብርን በተመለከተ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ብዝሃ ዘርፍ እንዲሸጋገር የተነደፈው ፖሊሲ በእጅጉ ውጤታማ ሆኗል። መንግስት ከህዝብ ጋር ተሳስሮ ለምት እንዲያመጣ ግልጽ አቅጣጫ የተቀመጠውም ከለውጡ ወዲህ ነው። ለአብነትም መንግስትና ህዝብ ተሳስረው በአረንጓዴ አሻራ አማካኝነት 48 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል ችለዋል። ለዚህ ስኬት ደግሞ ከ25 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ሳይታክቱ በነጻ በየ ዓመቱ ወጥተው ችግኞችን መትከል ችለዋል። ይህም የመንግስትና ህዝብ ቅንጅትን በተግባር ያሳየ ነው።
አምስቱ የሪፎርሙ ዓላማዎች:-
1) የተዛባ የኢኮኖሚ ስርዓትን ማረቅ
2) የንግድ ከባቢን ማሻሻል
3) የዘርፎች ምርታማነትና የመወዳዳር አቅም ማሳደግ
4) የማስፈጸም አቅምን ማሳደግ
5) ዘላቂ የፋይናንስ ስርዓት ማረጋገጥ

የእዳ ሽግሽግን በተመለከተ
ኢትዮጵያ አሁን ላይ እዳዋን ለመክፈል ምንም ችግር የለባትም። በሪፎርሙ አመካኝነት ከ4 አስከ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የእዳ ሽግሽግ ተደርጓል። ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎም መንግስት አንድም ዶላር የንግድ ብድር አልወሰደም። ይህም እዳን ለመቆጣጠር ያለንን ጽኑ አቋም ያሳያል።
ግብርናን በተመለከተ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም በሁሉም መመዘኛዎች ከፍተኛ ለውጥ በፍጥነት ማስመዝገብ እሏል። ለአብነትም ግብርና ብቻውን የ7 ነጥብ 3 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል። በምርት ደረጃም ሩዝን ወስደን ብናይ ከነበረበት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 63 ሚሊዮን ኩንታል ማሳደግ የተቻለ ሲሆን የስንዴ ምርትንም ከለውጡ በፊት ከነበረበት 47 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 280 ሚሊዮን ኩንታል በአጠረ ጊዜ ውስጥ አሳድግነዋል።

ገቢን በተመለከተ
ያለፈው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛ ገቢ ያገኘችበት ነው። ለአብነትም ከሸቀጦች ወጪ ንግድ 8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል። ከሬሚታንስ 7 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ የተገኘ ሲሆን ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትም በቢሊዮን ዶላር ማዳን ተችሏል። በዚህም የኢትዮጵያ ሪዘርቭ በ10 እጥፍ አድጓል።
የዋጋ ንረትን በተመለከተ
መንግስት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት 440 ቢሊዮን ብር ድጎማ አድርጓል። ከዚህም ውስጥ 160 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ለደሞዝ ጭማሪ ድጎማ የተደረገ ነው። ለነዳጅም 140 ቢሊዮን ድጎማ ተደርጓል። በዚህም የጥቅምት ወር የዋጋ ንረት 11 ነጥብ 7 ወርዷል። ይህም ከሪፎርሙ ዘመን ጀምሮ ትንሹ የዋጋ ንረት ሆኖ ተመዝግቧል። በቀጣይም ይህን አሃዝ ወደ አንድ አሃዝ ለማውረድ ይሰራል።
አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያን በተመለከተ
አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ ከ100 ሚሊዮን በላይ ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን፤ ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ በቻ ሳይሆን ትልቁ የአውሮፕላን ማረፊያ ባለቤት ያደርገዋል። ለዚህ ግዙፍ የ10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንትም ኢትዮጵያን በቀጣይነት የአፍሪካ የአቬሽን ማእከል ሆና እንድትቀጥል ያደርጋታል።
ሜጋ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ
ኢትዮጵያ ውስጥ በጋዝ፣ ማዳበሪያ፣ አውሮፕላን ማረፊያና ቤቶች ልማት ላይ የምንሰራው ስራ ጨዋታ ቀያሪ ነው። የማዳበሪያ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ብቻ የግብርና ምርታማነትን ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ ይቻላል። ይህም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ትልቅ እጥፋት ነው። ሌሎችም ሲጠናቀቁ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ይመጣል።
የኮሪደር ልማትን በተመለከተ
የኮሪደር ልማት የቦታና ጊዜ ምልከታን የሚቀይር ነው። ለአብነትም በአዲስ አበባ ብቻ ከአንድ ኚህ በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ተገንብቷል። በርካታ ወጣቶች ወደ ስፖርት እየተመለሱ ነው። ይህም ማህበረሰብን የመገንባት ስራ ነው። የትውልድ ስነ ልቦና ስብራትን እያረቀ ያለ ስራም ጭምር ነው። ይህን ማንም ሰው የሚያየው፤ ማንም ሰው የሚናገረው ጉዳይ ነው።

የፕሮጀክቶች ክትትልን በሚመለከት
ኢትዮጵያ ውስጥ 346 የመንገድ ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ ናቸው። በፌደራል መንግስት ብቻ 26 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር በፌደራል መንግስት ብቻ እየተገነባ ነው። እነዚህን ሁሉ ፕሮጀክቶች በተመሳሳይ መከታታል እጅግ አስቸጋሪ ስራ ነው። ግድብን በሚለከትም ከ200 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 14 መካከለኛና አነስተኛ የግድብ ፕሮጀክቶች አሉ። መንግስት የማስፈጸም አቅሙን በማሳደግ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እየሰራ ነው።
ከተረጂነት መላቀቅን በተመለከተ
ተሪጂነት የመስራት ጉልበትን የሚበላ ካንሰር ነው። በስንዴ፣ ፍራፍሬና ሌማት ትሩፋት የምንሰራው ስራም ከተረጂነት ለመላቀቅ ባለን ቁርጠኝነት ነው። ስለዚህ ጨከን ብለን ተረጂነት ይበቃናል ማለት አለብን። ደግሞም እንችላለን። እርዳታ ብዙ ጣጣ በውስጡ አለበት። ኢትዮጵያን መለመኛ ማድረግ መቆም አለበት።
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ዕድገት በሚመለከት
በኢትዮጵያ የመጣው የእሳቤ ለውጥ በርካታ እምርታዎችን አምጥቷል። ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2032 በአፍሪካ 2ኛ በ2036 ደግሞ ከአፍሪካ የመጀመሪያውን ኢኮኖሚ እንደምትገነባ ጥርጥር የለኝም
#የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia #EBC #ebcdotstream #Ethiopia #PMAbiy