Search

ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 714.7 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ከዕቅዷ በላይ አሳክታለች - ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 714.7 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ከዕቅዷ በላይ አሳክታለች ሲሉ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ይፋ አደረጉ።

በመርሐ ግብሩ የተሳተፈው ሕዝብ 29.7 ሚሊዮን መሆኑን ያነሱት ዶክተር ግርማ፣ የዛሬው ቀን የኢትዮጵያ ሕዝብ በኅብረት ታሪክ የሠራበት ዕለት እንደሆነ ተናግረዋል። 

በዚህም ኢትዮጵያውን ያሰቡትን እንደሚያሳኩ ያስመሰከሩበትን ውጤት በማስመዝገባቸው ሊኮሩ ይገባል ብለዋል።

መርሐ ግብሩን በማስተባበር እና በመሳተፍ ታሪክ ለሠሩት ኢትዮጵያውያን ሁሉ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል። 

"በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ እስከ አሁን ከመጣንበት ጉዞ አንጻር በቀሪው ጊዜ የታቀደው የ7.5 ቢሊዮን ዕቅድ እንደሚሳካ ማሳያ ነው ብለዋል።

በለሚ ታደሰ 

#GreenLegacy #700MillionTrees #PlantForEthiopia #MyTreeMyFuture #አረንጓዴዐሻራ