Search

የኃይል አማራጭ ይዞ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ያለው የትኛውም አካል ዓላማው ገቢር ነበብ አይደለም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ማክሰኞ ጥቅምት 18, 2018 131

ኢትዮጵያ ውስጥ የመገንጠልም ሆነ የመጠቅለል ዓላማን ይዞ መሣሪያ ያነሣ አካል ዓላማ ገቢር ነበብ እንዳልሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰላምን አስመልከቶ ከምክር ቤት የተነሣው ሐሳብ ተቀባይነት ያለው መሆኑን ጠቅሰው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የቆየውን ግጭት ማስቀረት ሁሉም የሚፈልገው ጉዳይ ነው ብለዋል።
ነገር ግን ኢትዮጵያ ሰላም ሆና እንዳትኖር ሀገራት እና እነሱ የሚጋልቧቸው ወገኖች አስካሉ ድረስ ችግሩ መቀጠሉ እንደማይቀር በመጠቆም፣ እንደዚህ ዓይነት ችግርን ለመፍታት ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ግልጽ አቋም መያዝ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የውጭ ጠላቶች ኢትዮጵያን ወግተው ማሸነፍ እንደማይችሉ ስለሚያውቁ፣ ‘በቀላሉ ሥልጣን አገኛለሁ’ የሚለውን ባንዳ ገዝተው እንደሚያሠሩ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያወሱት።
የትኛውም የኃይል አማራጭን ይዞ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀስ አካል ገቢር ነበብ እንዳልሆነ ጠቅሰው፣ ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ እነሱ ለሚፈልጉት መጠቅለልም ሆነ መገንጠል የማትመች መሆኗን ካለመረዳታቸው የመጣ እንደሆነ ገልጸዋል።
በጉጉት እና በመሻት የሚጋልቧቸው ፈረሶች እነዚህ አቅጣጫቸውን የማያቁ አካላትን እንደሚጠቀሙ ጠቅሰው፣ የጠላት መሣሪያ የሚሆኑት ሁሉ ማንን እንደሚገነጥሉም ሆነ ማንን እንደሚጠቀልሉ የማያውቁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
 
በለሚ ታደሰ