Search

ኢትዮጵያ ሲያምርባት ዐይኑ የሚቀላ ስለ ሰላሟ መጨነቅ አይችልም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ረቡዕ ጥቅምት 19, 2018 154

ኢትዮጵያ ሲያምርባት ዐይኑ የሚቀላ ስለ ሰላሟ መጨነቅ እንደማይችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።
"ሕዳሴ ሲያልቅ ሕዳሴ ምን ያስፈልጋል? ከሌሎች ጋር ያጋጨናል፤ የባሕር በር ጥያቄ ሲነሣ የሚሸማቀቅ፣ የሚያፍር፣ ደፈር ብሎ 130 ሚሊዮን ሕዝብ የባሕር በር ያስፈልገዋል ማለት የሚተናነቀው፤ ለኢትዮጵያ ጥቅም እና ፍላጎት ከጎኗ መቆም የማይሻ፣ ራሱን እንደማንጎ የሚቆጥር ግራዋ ነው" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
እንደዚህ ዓይነቱ የኢትዮጵያ ችግር የማይከፋው ወገን ራሱን ሲጠራ ‘ማንጎ ነኝ’ ይበል እንጂ መራር እንደሆነ ገልጸው፣ ማንም ሰው ራሱን በጠራበት ሳይሆን የሚለካው በፍሬው ነው ብለዋል።
የትናንቱ ገንጣይ አስገንጣይ ቡድን ታገለ ለመባል መጀመሪያ የሚያደርገው የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ መሆኑን መቀበል እንደሆነ ጠቁመው፣ የዛሬዎቹ ደግሞ "የባሕር በር ጉዳይ እኛን አይመለከተንም" ካላሉ የታገሉ አይመስላቸውም ብለዋል።
ይህ ደግሞ ከታሪክ ስህተት አለመማር እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል።
በለሚ ታደሰ