በቢሾፍቱ የሚገነባው የአውሮፕላን ማረፊያ መንግሥት ለአቪዬሽን ዘርፉ የሰጠዉ ትኩረት ማሳያ መሆኑን የአቪዬሽን ዘርፍ ፀሐፊ የሆኑት ፓይለት ዮናታን መንክር ገለፁ።
ፓይለት ዮናታን መንክር ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚያስገነባው አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ በዓመት ከ100 ሚሊዮን በላይ ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችል ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል።

አዲሱ ፕሮጀክት 10 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀው፤ ፕሮጀክቱ የአየር መንገዱን አቅም በማሳደግ ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነቱን እንደሚያሳድግም አንስተዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ለአቪዬሽን ዘርፉ በሰጠው ትኩረት የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አንስተዋል።
በኢትዮጵያ እንደዚህ አይነት ግዙፍ ፕሮጀክቶች መገንባታቸው አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ እና የቱሪስት ቁጥርን ለማሳደግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱም ገልፀዋል።
በቢታኒያ ሲሳይ