ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ትናንት ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሸዋ ዞን ጉብኝት አድርገዋል።
በጉብኝቱ የተሳተፉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ፥ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በተጀመረው ጉዞ ገጠሩን መቀየር ምን ዓይነት ለውጥ እያመጣ እንዳለ ተመልክተናል ብለዋል።

አብዛኛው የሀገሪቱ ኅብረተሰብ የሚኖረው በገጠር ነው ያሉት አፈጉባዔ ታገሠ፤ ሀገሪቱ ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና የጀመረችውን ጉዞ ለማፋጠን የገጠሩን ኅብረተሰብ የአኗኗር ዘይቤ መለወጥ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
በገጠራማ አካባቢዎች ምርትና ምርታማነትን አሳድጎ ወደ ኢንዱስትሪ በማሸጋገር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባም አመላክተዋል።

በዚህ አግባብ ገጠሪቱ ኢትዮጵያን ለመለወጥ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች አበረታች እና ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በጉብኝታቸው የተመለከቷቸው የስንዴ፣ ሩዝ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ማሳዎች ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ በትክክለኛ መስመር ላይ ስለመሆኗ ማሳያ ናቸው ብለዋል።
በሃይማኖት ከበደ
#ebcdotstream #ethiopia #agriculture
 
                                                 
                                                                 
                                                                 
                                                                 
                                                                 
                                            