Search

ኢትዮጵያ ከባሕር በር የተገለለችበት መንገድ ኢ-ፍትሐዊ እና ታሪካዊ ስህተት ነው

ዓርብ ጥቅምት 21, 2018 77

ኢትዮጵያ ከባሕር በር የተገለለችበት መንገድ ኢ-ፍትሐዊና ታሪካዊ ስህተት መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ ገለጹ፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ የባሕር በር ማጣት ከሸቀጥ ጋር ብቻ የተያያዘ ጉዳይ አለመሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
ይልቁንስ የኢትዮጵያን የፖሊሲ ነጻነት የሚጋፋ፣ ኢኮኖሚያዊ ጫና የሚፈጥር የሉዓላዊነት ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም መንግስት የባሕር በር ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ዓለም አቀፍ ሕጎችና አሰራሮችን በመከተል በሰላማዊና በሰጥቶ መቀበል መርህ የተመሰረተ አቋም መያዙን ተናግረዋል፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ መሰረት ኃይሌ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ የባሕር በር ተጠቃሚነት ጉዳይ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባሕር በር ለማግኘት እየሰራች መሆኑን ገልጸው፤ ጥረቷን አጠናክራ ትቀጥላለች ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር) ፤በዓለም አቀፍ ሕግና አሰራር የባሕር በር ያላቸው ሀገራት ለወደብ አልባ ሀገራት የባሕር ዳርቻ የመፍቀድ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዓላማ በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የባሕር በር ተጠቃሚ መሆን ነው ያሉት ፈትሂ (ዶ/ር)፤ የባሕር በርን ማሳካት ግዴታችን ነው ብለዋል፡፡