Search

የተሰበሰቡ አጀንዳዎች እንደ ቅደም ተከተላቸው ምክክር ይደረግባቸዋል - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ዓርብ ጥቅምት 21, 2018 57

በኢትዮጵያ ከወራት በኋላ እንደሚካሄድ የሚጠበቀው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ለዘመናት የቆዩ ችግሮችን የሚፈታ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
ሀገራዊ ምክክሩ ታሪካዊ፣ መዋቅራዊ፣ የማንነት እና በማህበረሰቡ የሚነሱ መሰረታዊ ችግሮች ላይ ተወያይቶ ትምህርት በመቅሰም መፍትሄ የሚገኝበት መሆኑን ኮሚሽነሩ ለኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ተናግረዋል።
በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሰበሰቡ አጀንዳዎችም ይህን የሚያመላክቱ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ እንደቅደም ተከተላቸው በጉባኤው ይመከርባቸዋል ብለዋል፡፡
ከምክክሩ በኋላም በሕዝቡ የሚሰጡትን የመፍትሄ ምክረ ሀሳቦች ለመንግስት እና ለአስፈፃሚ አካላት በማቅረብ፣ በሥራ ላይ እንዲውሉ ኮሚሽኑ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል፡፡
ሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማ እንዲሆን ኮሚሽኑ እንደ ሽምግልና ያሉ ሀገር በቀል እሴቶች እና እውቀቶችን መሰረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝም ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡
በተመኙሽ አያሌው