ኢትዮጵያ ከጥገኝነት እንዳትላቀቅ እና ያላትን ሀብት እንዳታለማ ተፅዕኖ ሲደረግባት ቆይቷል።
በውስጥ እና በውጭ ኃይሎች ሴራም ብሔራዊ ጥቅሟን በአግባቡ እንዳታስከብር ስትደረግ ኖራለች።
በውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት የአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ተመራማሪ የሆኑት አቶ ሽመልስ ኃይሉ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ከታሪክ እንደምናየው ኢትዮጵያ በውጭ እና በውስጥ ጠላቶቿ ተፅዕኖ ውስጥ በመግባት ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን እንድታጣ ሆናለች ብለዋል።
ሀገሪቱ በባንዳዎች ሴራ የባህር በር ባለቤትነቷን እንድታጣ የተደረገበት መንገድ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ሊሆን እንደሚችል ተመራማሪው አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ተቃራኒ የሆኑ የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች ሀገር ውስጥ ያለውን ጊዜያዊ ጥቅሞች በመውሰድ እና ለተለያዩ አመፅ እና ችግሮች ድጋፍ እንደሚያደርጉም ነው የገለፁት።
መንግሥታት ቢቀያየሩም ብሔራዊ ጥቅም የሚቀር ጉዳይ አለመሆኑን ያነሱት ተመራማሪው፤ ነገር ግን የሀገር ውስጥ ባንዳዎች ከውጭ ጠላቶች ጋር በማበር የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅምና የውጭ ዲፕሎማሲ ሲጎዱት እንደነበረ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ በግፍ ያጣችውን የባህር በር ባለቤትነት ለማስመለስ በትጋት እየሰራች እንደምትገኝ አንስተው፤ ሀገሪቱ ጀምራ የጨረሰችው እንደ ህዳሴ ግድብ ያሉ ፕሮጀክቶች የአይበገሬነቷ ምሳሌ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።
በሜሮን ንብረት
#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #national_interest #seaaccess