ኢትዮጵያ በታሪኳ የተለያዩ የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች ቢነሱባትም አንዳቸውም ግን አሸንፈዋት አያውቁም።
ዕድገቷን የማይሹ አካላት በጦርነት ሊያሸንፏት እንደማይችሉ ስለሚያውቁት ያላቸው አማራጭ ሰላሟን ለማደፍረስ ተላላኪ ባንዳ እና ባዳዎችን ማሰማራት ነው።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢው አምባሳደር ቶፊቅ አብዱላሂ (ዶ/ር)፥ ኢትዮጵያ በዘመኗ ሁሉ ጠላት ባታጣም ያሸነፋት ግን አለመኖሩን ነው የገለጹት።

አምባሳደር ቶፊቅ ከኢቲቪ አዲስ ቀን መሰናዶ ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ የዓባይ ወንዝ መነሻን ለመቆጣጠር የተለያዩ ሙከራዎች መደረጋቸውን አስታውሰዋል።
ኢትዮጵያ ባልተገባ መንገድ ከባሕር በሯ እንድትገለል መደረጓን አንስተው፤ የባሕር በር ጥያቄ ብሔራዊ ጥቅምን የማስከበር ጉዳይ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ግጭቶች እንዲበራከቱ እና ሰላም እንዲደፈርስ የሚሠሩ አካላት መኖራቸውን ጠቅሰው፤ ይህን በመመከት ረገድ በደንብ መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና የቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር እና ተመራማሪው ንጉሴ አደም (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ተለዋዋጭ በሆነው የዓለም ሥርዓት ውስጥ በሴራ ከባሕር በሯ የተገፋችው ኢትዮጵያ ሀብቷን መልሳ የማግኘት መብት አላት ብለዋል።
በሜሮን ንብረት
#ebcdotstream #ethiopia #seaport #redsea #nationalinterest