Search

የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ እና ዓለም አቀፍ ሕጎች

ዓርብ ጥቅምት 28, 2018 1396

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲን ያካተተው የአፍሪካ ምሥራቃዊ ክፍል የዓለም ኃያላን ዓይን ያረፈበት ቀጣና ነው።
የአፍሪካ ቀንድ ክልላዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኃይሎች ትልቅ የስበት ማዕከላቸው አድርገውታል።
ቀደም ሲል ይህን አካባቢ ዋና ትኩረታቸው አድርገው የነበሩት እንደ አሜሪካ እና ቻይና ያሉ “ኃያላን” ሲሆኑ፣ አሁን ግን የአፍሪካ ቀንድ ለአዳዲስ ተወዳዳሪዎች ወሳኝ የፉክክር ሜዳ ሆኗል። እንደ ሳውዲ ዓረቢያ፣ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ፣ ተርኪዬ፣ ኳታር፣ ኢራን እና ግብፅ በአፍሪካ ቀንድ ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ዋና ቀጣናዊ ተዋናዮች ሆነው ብቅ ብለዋል።

በአሁኑ ጊዜ አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ጃፓን፣ ቻይና፣ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ እና ቱርክን ጨምሮ 11 ሀገራት በቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ የጦር ሰፈር አላቸው፤ እዚህ የመገኘታቸው ምክንያት እንደየሀገራቱ ይለያያል። ይሁንና የቅርብ ጊዜ ጂኦፖለቲካዊ ክስተቶች የአካባቢውን ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ በማሳደጉ፤ ቀይ ባሕር ታላቅ የኃይል ሽኩቻ ምሕዋር መሆኑ ግልጽ ነው።

2 ሺህ 250 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የቀይ ባሕር ኮሪደር ሜዲትራኒያን ባሕርን እና ህንድ ውቅያኖስን አልፎ ወደ እስያ የሚገባው ቁልፍ የውኃ መስመር ሲሆን፤ በየዓመቱ በቢሊዮኖች የሚቆጠር የንግድ ልውውጥ ይከናወንበታል።

10 በመቶ በላይ የሚሆነው የዓለም ንግድ በየዓመቱ በቀይ ባሕር በኩል ያልፋል። የንግድ መስመሩ በዓለም ላይ ካሉት 10 እጅግ ስትራቴጂያዊ የውኃ መንገዶች ሁለቱን ማለትም በባሕሩ ደቡባዊ መግቢያ የሚገኘውን ባብ ኤል-ማንዴብ እና በሰሜን ግብፅ የሚገኘውን ስዊዝ ካናልን ያቋርጣሉ። ይህ የቀይ ባሕር አካባቢ በዘይት እና በከበሩ ማዕድናትም የበለፀገ ነው።

የማሪን ኢንሳይት (Marine Insight) መረጃ እንደሚያመላክተው በቀይ ባሕር ጠረፎች 10 ትላልቅ እና ሥራ የሚበዛባቸው ወደቦች አሉ። በቀይ ባሕር ዙሪያ ከሚገኙት ሥራ የሚበዛባቸው ወደቦች መካከል የጂዳ ወደብ አንዱ ሲሆን፤ በዓመት ወደ 52 ሚሊዮን ቶን ጭነት፣ 4 ሚሊዮን ኮንቴነሮች (TEU) እና 275 ሺህ 700 መንገደኞችን ያስተላልፋል።

በፖርት ሱዳን 8.6 ሚሊዮን ቶን ጭነት እና 431 ሺህ ኮንቴነሮች ይይተላለፋሉ። ሌላው ቀይ ባሕር ላይ የሚገኝ ወደብ የጂቡቲ ወደብ ሲሆን፤ 5.8 ሚሊዮን ቶን በላይ ጭነት እና 293 ሺህ ኮንቴነሮች (TEU) በዓመት ይተላለፉበታል። በምፅዋ ወደብ ደግሞ በዓመት 826 ሺህ ቶን ጭነት ያልፋል። 

የሳውዲ ዓረቢያ ንብረት የሆነው ያንቡ የንግድ ወደብ 1.8 ኪሜ ርዝመት ያለው ሲሆን፣ በዓመት 13.5 ሚሊዮን ቶን ጭነት የሚያስተናግዱ 12 ማረፊያዎች እና 1 ሺህ 500 መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችል ልዩ የመንገደኞች ተርሚናል አለው።

የግብፅ ንብረት የሆነው ሳፋጋ ወደብ 100 ሺህ ቶን የመጫን አቅም ያለው የእህል ሲሎ ያለው ሲሆን፣ በዓመት ወደ 742 መርከቦችን በማስተናገድ ከ3.8 ሚሊዮን ቶን በላይ ጭነት እና 876 ሺህ በላይ መንገደኞችን ያስተናግዳል።

የእስራኤሉ ኢላት ወደብ 2.1 ሚሊዮን ቶን ደረቅ ጭነት፣ 70 ሺህ መኪኖች እና 50 ሺህ ኮንቴነርች በየዓመቱ ያልፉበታል። ሆዴዳ ወደብ የየመን ንብረት ሲሆን፤ 1 ሚሊዮን ቶን የፔትሮሊየም ምርቶችን ጨምሮ 5.7 ሚሊዮን ቶን ጭነት ያስተናግዳል።

አሰብ ወደብ 1.2 ሚሊዮን ቶን ደረቅ ጭነት፣ 32 ሺህ ኮንቴነሮች (TEU) እና 1.3 ሚሊዮን ቶን ፈሳሽ ጭነት ይተላለፍበት እንደነበር መረጃዎች ያመላክታሉ

ሌላኛው የየመኑ ኤደን ወደብ በዓመት 2 ሺህ መርከቦች የማስተናገድ አቅም ያለው ሲሆን፣ 15.6 ሚሊዮን ቶን ጭነት እና 380 ሺህ ኮንቴነሮች (TEUs) በዚህ ይተላለፋሉ።

 

የባሕር በርን የተመለከቱ ዓለም አቀፍ ሕጎች

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የባሕር ሕግ አንቀጽ 69 ንዑስ አንቀጽ 1 እስከ 5፥ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት በአካባቢያቸው ካለው ባሕር የተፈጥሮ ሀብት እኩል የመጠቀም መብት እንዳላቸው ይደነግጋል። ይህም፣ ዓሳ ማጥመድን እና በባሕር ውስጥ ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶች ፍለጋን ጨምሮ ሌሎች ከባሕር ተፈጥሮ ሀብት ጋር የተያያዙ ሀብቶች ተጠቃሚነት መብትን ያካትታል።

የዚሁ ሕግ አንቀጽ 125 ንዑስ አንቀጽ 1 እንደሚያመለክተው፥ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት በአካባቢያቸው ያለውን ባሕር የመጠቀም እና የመሸጋገር ዓለም አቀፍ መብት አላቸው። ይህ መብት የባሕር በር በሌለው ሀገር፣ የባሕር በር ባለቤት በሆነው ሀገር እና በቀጣናው መካከል በሚደረግ ስምምነት ሊፈጸም እንደሚገባንዑስ አንቀጽ 2 ላይ ተመላክቷል።

አንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ ደግሞ፥ እነዚህ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት በስምምነት የተደረገ የተለየ የአገልግሎት ክፍያ ከሌለ በስተቀር ለተገለገሉበት ባሕር ምንም ዓይነት የትራፊክ ታክስ ወይንም ሌላ ክፍያ እንደማይጠየቁ ይደነግጋል።

የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በምስረታ ቻርተሩ መግቢያ ላይ በባሕር ሕግ ጉዳዮች ላይ ባሰፈረው ሀተታ፥ የአፍሪከ ሀገራት የባሕር በር ያላቸውን ጨምሮ ከባሕር ሊያገኙት የሚገባቸውን ጥቅም እያገኙ እንዳልሆነ ጠቅሶ፤ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት ከባሕር የመጠቀም መብታቸው ሊጠበቅ እንደሚገባ እና ይህም ከዓለም አቀፍ መርሕ አንጻር ሊታይ እንደሚገባው ይደነግጋል።

 

ኢትዮጵያ እና የባሕር በር ታሪካዊ ዳራ

የጎን ስፋቱ 50 እስከ 60 ኪሎ ሜትር የሚሆነውን ከመርሳ ፋጡማ ተነስቶ የትግራይን እና አፋርን ምድር እየታከከ ቁልቁል እስከ ራስ ዱሜራስ የሚወርደውን ቀጭን መሬት ያየ ሁሉ፣ የጣሊያን ቅኝ ገዢዎች ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር የሚያስወጣ መሬት እንዳይኖራት ሆን ብለው ያጠሩት አጥር ይመስላል።

ኢትዮጵያ ይህን አጥር አፍርሳ ኤርትራን ለመቀላለቀል የዲፕሎማሲ ዘመቻ ባካሄደችበት እና ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባኤ ጥያቄ ባቀረበችበት ወቅት የባሕር በር እንድታገኝ የሚያስችል መሬት ተፈቅዶላት እንደነበረ ያዕቆብ ኃይለማርያም (/) “አሰብ የማን ናት?” በሚለው መጽሐፋቸው ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ የወቅቱ ጥያቄ መላዋን ኤርትራ ከኢትዮጵያ ማዋሃድ ስለነበር ተለይቶ የተሰጣትን የባሕር በር የማግኘት አማራጭ አልተቀበለችውም ነበር።

ክርክሩ እና የዲፕሎማሲ ዘመቻው ፍሬ አፍርቶ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን እንድትቀላቀል ተወስኖ ኢትዮጵያም ዳግም የባሕር ጠረፍ ባለቤት ሆና ነበር።

እንደ ያዕቆብ ኃይለ ማርያም (/)፥ በወቅቱ የነበሩት መንግሥታት በፌዴሬሽኑ አያያዝ ላይ በተከታታይ በፈፀሙአቸው ስህተቶች ፌዴሬሽኑ ፈርሶ በተካሄደው ጦርነት ብዙ ደም ፈሶ ኤርትራ ነጻ ሀገር እንድትሆን በተፈቀደበት ወቅትም ኢትዮጵያ ሕጋዊ የባሕር በር ባለቤትነቷን እንዳታቀርብ በወቅቱ የነበሩት መሪዎቿ ተቃውመው ባዶ እጇን አስቀርተዋታል።

 

ቀይ ባሕር አካባቢ እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎች እና ቀጣይ የአካባቢው ዕጣ ፈንታ

ከላይ እንደተጠቀሰው አሜሪካ እና ቻይናን ጨምሮ በርካታ ሀገራት በቀይ ባሕር አካባቢ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በትኩረት ከመከታተል አልፎ የጦር ሰፈሮቻቸውን አቋቁመው በአካባቢው ያላቸውን ዓለም አቀፍ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሱ ነው። እነዚህ ሀገራት አድማስ ተሻግረው እዚህ ሲገኙ ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመጥቀስ እና በአካባቢው ያለው ያልተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታ በዓለም ላይ ሊፈጥር ይችላል ያሉትን ቀውስ ምክንያት በመስጠት ነው።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግምት መሠረት በቀይ ባሕር ዙሪያ ያለው የሕዝብ ብዛት .. በ2050 . 343 ሚሊዮን ይደርሳል።

የቀጣናው የሕዝብ ቁጥር እያሻቃበ ባለበት በአሁኑ ወቅት በአካባቢው የሚፈጠሩ ቀውሶች ዳፋ ድንበር ተሻግረው አውሮፓ የሚደርሱ ናቸው። በመሆኑም አውሮፓን ከመካከለኛው ምሥራቅ እና ከሩቅ ምስራቅ ጋር የሚያገናኘው ቀይ ባሕር እና 1 ሺህ . ርዝመት ያለው የባሕሩ ክፍል ሰላሙ እንዲጠበቅ የአካባቢው ሀገራትን ተሳትፎ ይፈልጋል።

በአሜሪካውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት 24 ዓመታት ያገለገሉት እና በአሁኑ ጊዜ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የዓረብ ማዕከል (Arab Center Washington DC) ተባባሪ ባልደረባ የሆኑት ቻርልስ ዱኔ እንደሚሉት፥ ቀይ ባሕር ወሳኝ የኢኮኖሚ የደም ቧንቧ ሲሆን፤ ተፈላጊነቱ በመጪዎቹ ዓመታትም ከዚህ በላይ እየጨመረ ሊሄድ ይችላል። በጂኦፖለቲካዊ አገላለጽ፣ ምናልባት ከአሜሪካ እናአውሮፓ ፖሊሲ አውጪዎች ነባራዊየመካከለኛው ምሥራቅትኩረት የበለጠ አካታች የፖሊሲ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ሆኖ መታየት አለበት ይላሉ።

በአካባቢው ያለው የአፍሪካ ክፍል በመሠረተ ልማት እጥረት እና በምጣኔ ሀብት ዕድገት ኋላ ቀር ቢሆንም፣ የቀጣናው አቅም እያደገ እና የሕዝብ ቁጥሩ እየጨመረ ሲመጣ በቀይ ባሕር አካባቢ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ፍላጎት፣ የትጥቅ ግጭቶች እና የፖለቲካ አለመረጋጋቶች እየሰፉ እንደሚሄዱ ተንታኞች ይገልጻሉ።

እነዚህን ዓለም አቀፍ ነባራዊ እና መጻኢ ሁኔታዎችን በመተንተን በቀይ ባሕር አካባቢ የሚያንዣብቡ ሀገራት ግን በአፍሪካ ቀንድ ስትራቴጂያዊ አቀማመጥ ላይ የምትገኘውን እና አካባቢውን አስተሳስሮ ለመያዝ ትልቅ ሚና እየተጫወተች ያለችውን ኢትዮጵያን ይዘነጋሉ።

ከ7 ዓመታት በፊት በነበረው የሀገሪቱ አመራር ዳተኝነት እና በጉዳዩ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ማዳፈን የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ወደ ፊት እንዳይመጣ ያደረገ ዋነኛው ምክንያት ነበረ። ሌሎች ሀገራትም ይህን የኢትዮጵያን መዘናጋት በመጠቀም በአካባቢው ላይ የተለያዩ ጥምረቶችን እየፈጠሩ ይገኛሉ። ለአብነትም በሳውዲ ዓረቢያ አስተባባሪነት የተመሰረተው “The Red Sea Forum/Alliance” የሚጠቀስ ነው።

ስምንት ሀገራትን ያቀፈው እና እ.አ.አ በጥር 2020 በሳውዲ ዓረቢያ አንቀሳቃሽነት የተመሰረተው “The Red Sea Forum/Alliance” ሲቋቋም ኢትዮጵያን እና ሌሎች የጉዳዩ ባለቤቶችን ማግለሉ ፍትሐዊ ካለመሆኑም በላይ የጥምረቱን ውጤታማነት ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባ እንደሆነም ይገለጻል።

ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ 120 ሚሊዮን በላይ ሲሆን፤ ይህም ኢትዮጵያን በዓለም የባሕር በር ከሌላቸው ሀገራት ከፍተኛ የሕዘብ ብዛት ያላት ሀገር ያደርጋታል። በአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ 17 ሀገራት የባሕር በር የሌላቸው ሲሆን፤ በእነዚህ ሀገራት ከሚኖረው አጠቃላይ ሕዝብ አንድ ሦሥተኛው የሚገኘው በኢትዮጵያ ነው። ይህ ሁኔታ ደግሞ በቀጣይ በአካባቢው ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ ቀላል ባለመሆኑ ኢትዮጵያን ያካተተ የጋራ ተጠቃሚነት ላይ መሥራት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው።

 

ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝባቸው ሕጋዊ መሠረቶች

ከላይ የተጠቀሱት ዓለም አቀፍ ሕጎች እና የአፍሪካ ሕብረት ድንጋጌዎች ኢትዮጵያንም የሚመለከቱ ናቸው። ኢትዮጵያ የምትገኝበት ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የአፍሪካ ቀንድ ሲሆን፤ ይህም የጂቡቲ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የባሕር ዳርቻን ያጠቃልላል። በሱዳን እና በኬንያ በኩል ያለው መስመርም ሌላው የባሕር በርን ለመጠቀም የሚያስችላት አማራጭ መንገድ ነው።

በሌላ አነጋገር የመንሥታቱ ድርጅት 1982 ባወጣው የባሕር ሕግ አንቀጽ 69 እንዲሁም ከአንቀጽ 125 እስከ 132 የተጠቀሱት ድንጋጌዎች እና አንቀጽ 148 የኢትዮጵያን የባሕር መውጫ መብት የሚመለከቱ ናቸው።

1900 1902 እና 1908 በኢትዮጵያ እና የኤርትራ ቅኝ ገዢ በነበረችው ጣሊያን መካከል የተደረጉት ስምምነቶች እና የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት 1964 የቅኝ ግዛት ውሎችን ማጽናቱ ለኢትዮጵያ የባሕር መውጫ መጥፋት ዋና ዋና ምክንያቶች እንደሆኑ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ መምህሩ ዳምጠው ተሰማ “International Law and Ethiopia’s right to access to the Sea outlet” በሚለው ጥናታዊ ጽሑፋቸው ጠቅሰዋል፤ ምሁሩ እነዚህ ስምምነቶች ቢኖሩም በሌላኛው ወገን በመጣሳቸው ሕጋዊ ተፈጻሚነት እንደሌላቸው በማስረጃ አስደግፈው አስቀምጠዋል።

ተመራማሪው ስምምነቶቹ ሕጋዊነት የሚያጡባቸውን መሠረቶችም ሲጠቅሱም ጣሊያን .. 1935 ኢትዮጵያን ዳግም ስትወር የመጀመሪያውን ስምምነት መጣሷን ይገልጻሉ። በዚህ ረገድ የቪዬና የስምምነት ሕግ አንቀጽ 60 (1) የሁለትዮሽ ውል በአንደኛው አካል መጣስ ሌላው አካል ለውሉ እንዳይገዛ እና ውሉን የጣሰውን አካል እንዲከስስ መብት ይሰጠዋል።

በዚህም መሰረት 1900 1902 እና 1908 ስምምነቶች በሌላኛው አካል ስለተጣሱ ተፈጻሚነት እንደሌላቸው ኢትዮጵያ ተከራክራለች፤ ይህ ደግሞ የአልጀርሱንም ስምምነት ዋጋ ያሳጣዋል።

በተጨማሪም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 1950ዎቹ ምክረ ሃሳብ እና የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ዳግም በኮንፌዴሬሽን መዋሀድየኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኘት መብትለመጠየቅ መሠረት ሊሆን የሚችል ስምምነት ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል መምህር ዳምጠው በጥናታዊ ጽሁፋቸው አመልክተዋል፤ እንደዚህ ዓይነቶቹ ተጨባጭ እውነታዎች እና ዓለም አቀፍ የሕግ ድንጋጌዎች የአልጀርሱ ስምምነት ሕጋዊ መሠረት እንደገና እንዲገመገም ጥያቄ እንደሚያስነሳም ጠቁመዋል።

 

ከእነዚህ ሕጋዊ መሠረቶች በመነሳትም

ከ5 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ሲመጣ በቅድሚያ ከተከናወኑት ሥራዎች ውስጥ አንዱ የባሕር ኃይል መመስረት ነው። ከፈረንሳይ እስከ ዱባይ ለባሕር ኃይል ሥልጠና ድጋፍ በማፈላለግ የባሕር ኃይልን እንደገና ያደራጀችው ኢትዮጵያ፣ 27 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የባሕር ኃይል አድሚራል በመሾም ኃይሉን አጠናክራለች።

ኢትዮጵያ የምታምነው የባሕር በርም ሆነ የቀይ ባሕር ጉዳይ ከኤርትራም፣ ከጂቡቲም፣ ከሶማሊያም፣ ከሱዳንም የገዘፈ የዓለም አቀፍ የጂኦ-ፖለቲካል እና የፖለቲካል ኢኮኖሚ ጉዳይ መሆኑን ነው። ቀይ ባሕር ከሜዲትራኒያን ባሕር እስክ ህንድ ውቅያኖስ ጫፍ፤ ከገልፍ እስከ አፍሪካ ቀንድ ያለውን አካባቢ የሚያካትት ነው። ስለሆነም ጉዳዩ በጥንቃቄ እና በሰጥቶ-መቀበል (Give-and-Take) መርሕ የሚከናወን እንጂ ጦር በመስበቅ የሚደረግ አይደለም።

ያዕቆብ ኃይለማርያም (/) እንደጠቀሱት ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝባቸው ነባራዊ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

F ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመጠቀም በቅርቧ የሚገኘውን የባሕር በር የማግኘት መብቷን ማስከበር፣

F ኢትዮጵያ የባሕር በር እንደምትፈልገው ሁሉ የባሕር በር ያላቸው የአካባቢው ሀገራት የእርሻ መሬት እና ሌሎች የሚያስፈልጋቸው ነገሮች ስላሉ፤ እነዚህን በመለዋወጥ ሰጥቶ የመቀበል መርህን ተግባራዊ በማድረግ፣

F ሀገራቱ ወደቦቹን እኩል በማልማት የሚጠቀሙባቸውን ጣምራ ሉዓላዊነት (joint sovereignty) በመፍጠር በጋራ መጠቀም የሚሉት ሲሆኑ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ደጋግመው እንደገለጹት ኢትዮጵያም ከነዚህ የሰጥቶ መቀበል አማራጮች ውጭ የመሄድ ዓላማ የላትም።

 

በለሚ ታደሰ