በ37ኛ ሳምንት የሊጉ መርኃ ግብር መቐለ 70 እንደርታ በኢትዮጵያ ቡና 3 ለ 0 መሸነፉን ተከትሎ፤ ከአርባምንጭ ከተማ በመቀጠል ከሊጉ የተሰናበተ ሁለተኛው ክለብ ሆኗል።
ዲቫይን ዋቺኩዋ (በፍፁም ቅጣት ምት) እንዲሁም ቢኒያም ጌታቸው (2) የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።
ተሰናባቹ መቐለ 70 እንደርታ በ37 ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ቡና ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ ከፕሪምየር ሊግ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱን አረጋግጧል።
በ2010 የውድድር ዓመት ወደ ፕሪምየር ሊጉ አድጎ ላለፉት ዓመታት በዋናው ሊግ ሲሳተፍ የቆየው መቐለ 70 እንደርታ፤ በ2011 የሊጉ ሻምፒዮን መሆን ችሎ ነበር።