Search

የሶሪያ ፕሬዚዳንት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አሜሪካ ገቡ

እሑድ ጥቅምት 30, 2018 223

የሶሪያ ፕሬዚዳንት አሕመድ አል-ሻራ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አሜሪካ ገብተዋል።
አሕመድ አል-ሻራ በዋይት ሐውስ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር በሚደረገው ውይይትም በሶሪያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የሚከናወኑ ጥረቶችን እንዲሁም አሜሪካ ከሶሪያ ጋር የሚኖራትን ትብብር የተመለከቱ ጉዳዮች አጀንዳ ሆነው እንደሚቀርቡ ይጠበቃል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ፕሬዚዳንት አሕመድ አል-ሻራ በሶሪያ መልሶ ግንባታ ዙሪያ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩም የሶሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል።
 
በመሐመድ ፊጣሞ