Search

ቡና በሀላባ ዞን

በሀላባ ዞን ባለፉት 3 ዓመታት 2 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ቡናን ማልማት መቻሉን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለፀ።

የመምሪያው ምክትል ኃላፊና የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ ሁሴን ሮባ እንደገለፁት፤ የሀላባ ዞን ዝናብ አጠር የሚባል በመሆኑ ከዚህ ቀደም የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት በብዛት አይታወቅም ነበር።

ባለፉት 3 ዓመታት በአርሶ አደሩ ዘንድ ግንዛቤ መፍጠር በመቻሉ 2 ሺህ ሄክታር መሬት በቡና መሸፈኑን አንስተው፤ ከዚህ ውስጥ 600 ሄክታሩ ምርት መስጠት መጀመሩን ገልጸዋል።

በሚቀጥሉት ዓመታት የዞኑን የቡና ሽፋን ወደ 20 ሺህ ሄክታር ለማሳደግ መታቀዱንም ገልፀው፤ በተለይም ከዚህ ቀደም በባሕር ዛፍ ተሸፍነው የነበሩ መሬቶችን ወደ ቡና የመቀየር ዘመቻ ተጀምሯል ነው ያሉት።

በዚህ ዓመትም በልግን ጨምሮ 640 ሺህ በላይ የቡና ችግኝ መተከሉን ጨምረው ተናግረዋል።

በእንቻለው አያሌው