Search

138 ፕሮጀክቶች የቀረቡበት የተማሪዎችና የመምህራን የፈጠራ ሥራ ውድድርና አውደ-ርዕይ

ሰኞ ኅዳር 01, 2018 257

በትምህርት ሚኒስቴርና አጋር ድርጅቶች አዘጋጅነት የተሰናዳው 10ኛው ሀገር አቀፍ የተማሪዎችና የመምህራን የፈጠራ ሥራ ውድድር በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ዛሬ በይፋ ተከፍቷል፡፡
መርሐ ግብሩን የከፈቱት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ፤ መንግሥት ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
የዓለም የሳይንስ ቀንን አስመልክቶ እየተካሄደ የሚገኘው የፈጠራ ሥራ ውድድርና አውደ-ርዕይ በክህሎትና በእውቀት የዳበረ ችግር ፈቺ ትውልድ ለማፍራት አጋዥ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
በዘንድሮው ውድድር ከመላው ኢትዮጵያ የተወጣጡ 138 ፕሮጀክቶች የቀረቡ ሲሆን፤ እስከ ኅዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የውድድሩን አሸናፊዎች ለመለየት የፈጠራ ሥራዎቹ ይመዘናሉ ተብሏል።
 
በመሐመድ ራሕመቶ