ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሸሪፍ ባስተላለፉት መልዕክት፥ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ዘላቂ የወንድማማችነት መንፈስ እጅግ ጠንካራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፓኪስታኑ አቻቸው ላቀረቡት ሞቅ ያለ የደስታ መግለጫና መልካም ምኞት ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ ሁለቱም ሀገራት የየራሳቸውን የሪፎርምና የማገገም የለውጥ ጎዳናዎች እያሳኩ ባሉበት በዚህ ወቅት ለብልጽግና እና ለዕድገት ባላቸው ቁርጠኝነት በአንድነት እንደሚቆሙ አስታውቀዋል፡፡
አያይዘውም የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ይበልጥ ለማሳደግና ሁለቱ ሀገራት ለመገንባት በጋራ የተስማሙበትን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር በጉጉት እንደሚጠብቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋዊ መልዕክታቸው አረጋግጠዋል፡፡