በስኮትላንድና በአሜሪካ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች በዓለም ለመጀመሪያ ግዜ በሮቦት የታገዘ የስትሮክ ቀዶ ሕክምና ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
ቀዶ ህክምናውን የስኮትላንድ ዱንድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ኢይሪስ ግራንዋልድ እና በአሜርካ ፍሎሪዳ የሚገኙት ዶክተር ሪቻርድ ሀኔል በሮቦት ማሽን በመታገዝ ማከናወናቸው ተጠቅሷል፡፡
በሮቦት የታገዘውን የቀዶ ሕክምና ሂደት ከዩኒቨርሲቲው አንድ ማዕከል ላይ ሆነው ሲከታተሉ የነበሩት ፕሮፌሰር ኢይሪስ፤ የሮቦት ማሽኑ ከዩኒቨርሲቲው አንድ የህክምና ምርምር ማዕከል ላይ ሆኖ ስራውን እንዲያከናውን መደረጉን ገልፀዋል፡፡
ዶክተር ሪቻርድ ሀኔል ደግሞ ከአሜርካ ፊሎሪዳ ከ6 ሺህ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሆነው በሮቦት ማሽኑ እገዛ የተሳካ የስትሮክ ቀዶ ህክምና ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡

በሮቦት ማሽን የታገዘው የስትሮክ ቀዶ ሕክምና በቀጣይም በተማሚዎች ላይ በደንብ ተግባራዊ ሲደረግ ለዘርፉ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር የህክምና ቡድኑ በሰጠው ገለጸ ተመላክቷል፡፡
የሮቦት ማሽኑ ያደረገው የቀዶ ሕክምና የታካሚውን የደም ዝውውር ጤናማ እንዲሆን በማድረግ ተማሚው በፍጥነት የሚያገግምበት፣ የተለየ ህክምና በመስጠት የሰውን ህይወትን መታደግ የሚያስችል የሕክምና ምርምር ውጤት የተገኘበት ነው ተብሏል፡፡
ባለፈው ወር ተግባራዊ ተደርጎ ውጤታማነቱ የተረጋገጠው በሮቦት ማሽን የታገዘው የስትሮክ ህክምና ሙከራ የሁለት ሀገራት የምርምር ቡድኖች የተሳተፉበት ሲሆን፤ ሮቦት ማሽኑን በማምረት ሴንታት የተባለ ኩባንያ እንዲሁ የአጋዥነት ሚናውን መወጣጡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በመሐመድ ፊጣሞ