Search

በአንድ ወቅት “የመናፍስት ዋሻ” የተባለውና ከፕሬዝደንት ሃርዲንግ እስከ ፕሬዝደንት ኦባማ የዘለቀው የአንድ ክፍለ ዘመን ፕሮጀክት

ቅዳሜ ኅዳር 06, 2018 1272

ይህ 2.9 .ሜትር ርዝመት ያለው የምድር ውስጥ ባቡር መስመር ፕሮጀክት  በበርካታ የፖለቲካ ትርምሶች የኢኮኖሚ ውድቀቶች እና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ አልፏል። እንዲህም ሆኖ ታዲያ ዛሬ በታቀደ 92 ዓመቱ የተጠናቀቀ የኒውዮርክን የማያቋርጥ የዕድገት ፍላጎት የሚያሳይ አስገራሚ  የምህንድስና ታሪክ ያለው ፕሮጀክት ነው።

1920ዎቹ መጨረሻ በይፋ የታቀደው ይህ የኒውዮርክ ሁለተኛ አቬኑ የምድር ውስጥ ባቡር መስመር ግንባታ ከፕሬዝዳንት ዋረን . ሃርዲንግ ዘመን ጀምሮ አስከ ፕሬዝዳንት ኦባማ  የአስተዳደር ዘመን ድረስ የዘለቀ የትውልድ ቅብብሎሽን የሚያሳይ ታሪክ ነው።

በወቅቱ አሜሪካንን ይመሩ በነበሩት በፕሬዝደንት ዋረን . ሀርዲንግ የስልጣን ዘመን የታቀደው ይህ ፕሮጀክት ከሳቸው በኋላም በነበሩት ፕሬዝደንቶች በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሳይጀመር ቆይቷል።

ከዛ በኋላም በፕሬዝዳንት ፍራንከሊን . ሩዝቬልት ዘመን በተካሄደው የሁለተኛው የአለም ጦርነት ምክንያትና ጦርነቱን ተከትሎ በተከሰተው የሀብት አጥረት ሳይጀመር ቀርቷል። በእርግጥ ይህ ብቻ አልነበረም ምክንያቱ በፕሬዝዳንት አይዘንሃወር እና ትሩማን ዘመን  ትኩረት የተደረገው  ዋና ዋና አውራ ጎዳናዎችን በመገንባት ላይ በመሆኑ ይህ የምድር ውስጥ ባቡር መስመር  ስራው ሳይጀመር እንዲቆይ ምክንያት ሆኗል።

ከእነዚህ ፕሬዝደንቶች ቀጥሎ ወደ ስልጣን በመጡት መሪዎች ዘመንም የአሜሪካ ኢኮኖሚ እየተሻሻለ ቢመጣም ይህንን ግዙፍ ፕሮጀክት ለማስጀመር የሚያስችል ሁኔታ ሳይፈጠር ቆየ።  በጥቂት አመታት ተጠናቆ ስራው ይጀመራል የተባለለት የሁለተኛው አቬኑ የባቡር መስመር ግንባታን ለመጀመር ያልፈለገ መሪ አልነበረም ግን አስቻይ ጉዳዮች ሳይኖሩ በመቅረታቸው በዚህ ፕሮጀክት ምክንያት የልቡ የሞላለት መሪ መሻቱ የተሳካላት አመራር ሳይኖር ቀረ

በመጨረሻ ግን 1972 በፕሬዝዳንት ሪቻርድ ኒክሰን የስልጣን ዘመን ትኩረትም አግኝቶ ጊዜውም ሆኖ ግንባታውን ለመጀመር የሚያስችል የገንዘብ ድጋፍ በመገኘቱ ስራው ተጀመረ።

በዚህ እለት የታተመው የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣም በፊት ገፁ ላይ ለመገንባት ከታቀደ 52 ዓመታት በኋላ ስራው ስለተጀመረው የሁለተኛው አቬኑ  የባቡር መስመር ግንባታ ስራ መጀመሩን የሚያበስር ይዘት ያለው ሀተታ ይዞ ሲወጣ እንዲህ የሚል ነበር፦

"የኒውዮርክ ከተማ 1920ዎቹ ጀምሮ ለመገንባት ስትታገልበት የኖረችው በምስራቅ ማንሃታን ላይ የነበረውን የትራንስፖርት ቀውስ ለመፍታት ያግዛል የተባለውን የምድር ውስጥ ባቡር መስመር ፕሮጀክት  በከተማዋ ገዥ ኔልሰን . ሮክፌለር እና በኒውዮርክ ከንቲባ ጆን . ሲንሳይ የመሰረት ድንጋዩ ተጥሎ ስራው ተጀመረ" የሚል ረጅም ዘገባ በፊት ገጽ ይዞ ነው ወጣ።

በወቅቱ በዓለም ላይ አጅግ በጣም ከተጨናነቁ የባቡር መስመሮች መሀከል አንዱ የነበረውን የኒውዮርክ ከተማ የትራፊክ መጨናነቅ ለማስወገድ መፍትሄ እንደሚሆን ታምኖበት ስራው የተጀመረው ይህ የሁለተኛው ጎዳና የመሬት ውስጥ ባቡር መስመር አቅዱ የወጣው 1920ዎቹ ነበር።

ይህ ወቅት አሜሪካ በከፍተኛ የኢኮኖሚ አለመረጋጋት ውስጥ የነበረችበት ጊዜ በመሆኑ ይህ ፕሮጀክት ወደ ስራ ሳይገባ አመታት ማለፍ ጀመሩ።

የኒውዮርክ ማንሃታን የትራንስፖርት ችግርም ግማሽ ዘመናትን ተሻግሮ 52 አመታት ተቆጠሩ፡፡ እንግዲህ ከዚህ በኋላ ነው የአሜሪካን ኢኮኖሚ ጠንክሮ ይህን ፕሮጀክት ለመገንባት ዝግጁ መሆኑ ሲታወቅ ከግማሽ ከፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረው የሁለተኛው ጎዳና የባቡር መስመር የግንባታ አቅድ አቧራውን አራግፎ በተግባር ላይ ሊውል የመሰረት ድንጋይ ተጥሎ ስራው የተጀመረው።

ስራው ከተጀመረ በኋላም መሐንዲሶች በሁለተኛ አቬኑ ጎዳና ስር የሚገኘውን የውስጥ ለውስጥ መስመር እየቆፈሩ ረጅም የዋሻ መንገድ ተሰራ።

በዚህ መልኩ ስራው እየተከናወነ እያለ ግን አሜሪካን 1970ዎቹ አጋማሽ ላይ ባጋጠማት የኢኮኖሚ ውድቀት ምክንያት ግንባታው ሙሉ በሙሉ ቆመ።

 እነዚህ 1970ዎቹ የተቆፈሩት ዋሻዎች በፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር፣ ሮናልድ ሬገን፣ በደብልዩ ቡሽ አና በፕሬዝደንት ቢል ክሊንተን ዘመን ግንባታቸው ሳይጀመር 32 ዓመታት ያህል ተዘግተው ቆዩ።

በዚህ ወቅት ነው ያላንዳች እንቅስቃሴ ተቆፍረው የተተውት የምድር ውስጥ የባቡር መስመሮች "የመናፍስት ዋሻየሚል ቅፅል ስም የተሰጣቸው።

በዚህ ላይ እያለም በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የህዝብ ብዛት ማስተናገድ የተሳነውን የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ለማቃለል እንዲያስችል ስራው ተጀምሮ 32 አመታት ተዘግቶ የቆየው የሁለተኛው ጎዳና የምድር ውስጥ ባቡር ግንባታ በፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብልዩ ቡሽ አስተዳደር ዘመን 2007 . ተነቃቅቶ አንደገና ስራው ተጀመረ።

አቅዱ ከወጣ በኋላ በአቅም ውሱንነት ምክንያት 52 አመታት ሳይጀመር የቆየው ከተጀመረም በኋላ በተለያዩ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ሲቆም እንደገና ሲጀመር አመታትን ያስቆጠረው ይህ ፕሮጀክት 2007 ስራው ከተጀመረ በኋላ መሻሻል ያለባቸውን ዲዛይኖች በማሻሻልና በዓለም ትልቁን የዋሻ መቆፈሪያ ማሽን  በስራ ላይ በማዋል ለውጤት ሰማብቃት ቀን ከሌት መስራት ተጀመረ።

4.4 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በጀት ተመድቦለት ዘመናዊነትን ባካተተ መልኩ እየተሻሻለ ስራው የቀጠለው ይህ የኒውዮርክ ማንሀታን የምድር ውስጥ ባቡር መስመር በከፍተኛ ወጭ እና የረቀቁ የግንባታ መሳሪያዎች በመታገዝ ከፕሬዝደንት ጆርጅ ቡሽ በኋላ  ለስምንት አመታት አሜሪካንን በመሯት በፕሬዝደንት ባራክ አባማ ዘመነ መንግስትም ቀጥሎ 96ኛ፣ 86 እና 72 የተባሉት የባቡር መስመሮች ከአስር አመታት ያልተቋረጠ ግንባታ በኋላ በጥር ወር 2017 ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ከፍት ሆኑ።

እጅግ ባማረ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በውስጡ በማካተት የተሰራው  ፕሮጀክት በአጭር መስመር ከፍተኛ ወጭ የወጣበት የአለማችን ውድ የዋሻ ውስጥ መንገድ መሆን ቻለ።

ይህ ለአመታት የዘለቀው የኒውዮርክ የምድር ውሰጥ ባቡር ጣቢያ ፕሮጀክት አሁንም አልቆመም እስከ ሀርለም ጫፍ የሚደርሰውን ሁለተኛውን ፕሮጀክት ለመጀመር የሚያስፈልገው በጀት ፀድቆ ስራውን ለመጀመር ጥናቶች እየተካሄዱ ይገኛሉ።

መደምደሚያ፦

የሁለተኛ አቬኑ የምድር ውስጥ ባቡር ፕሮጀክት ትርጉሙ ከቀላል የትራንስፖርት መስመር በላይ የሆነና 98 ዓመታት የዘለቀ የማያቋርጥ የጽናት መታሰቢያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው።

አቅዱ ሳይተገበር ለአምሳ ሁለት አመት የቆየው 1970ዎቹ ስራው ተጀምሮ ዋሻዎች ከተቆፈሩ በኋላ 32 ዓመታት ተረስተው በመቆየታቸው "የመናፍስት ዋሻዎችእስከመባል የደረሰው በመጨረሻም በአለም ውድ የተባለ በጀት ተመድቦለት የተጠናቀቀው ይህ ፕሮጀክት ከትውልድ ትውልድ የዘለቀ በብዙ ተግዳሮቶች አልፎ ለውጤት መብቃት የቻለ የመልማት ፍላጎት ተምሳሌትም ነው።

በውስጡ ሙዚየሞችን አካቶ የተገነባው እጅግ ዘመናዊ የምድር ውስጥ የባቡር መስመር ግንባታ ምንም እንኳን የመጀመሪያው ምዕራፍ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ቢጀምርም በቀጣይ ወደ ሰሜን ሃርሰም አና ደቡብ ወደ ፊናንስ ዲስትሪክት ለማራዘም አቅድ ተይዞ ይህንን ቀጣይ ፕሮጀክት ለመገንባት ጥናቶች እየተካሄዱ ይገኛል።

በዓለም ላይ ታላላቅ ህልሞች በአንድ ሰው ወይም በአንድ ትውልድ ሊታሰቡ ወይም ሊጀመሩ ይችላሉ። ሂደቱን እና ማጠናቀቁን የሚረከብ አስተዋይ እና ከዋናው ዓላማ የማይዛነፍ ትውልድን ግን የሚጠይቅ ነው። ለዚህም ነው እንዲህ ያሉ ፕሮጀክቶች በብዙ ትውልዶች ተስፋና በብዙ መሪዎች የማይናውጽ አቋም ህያው ሆነው የምናየው።

 

ዛሬ ይህ ፕሮጀክት ተጠናቆ የሚመላለሱበት ሰዎች ስለዘመናዊነቱ እና ስለባቡሮቹ ፍጥነት ወይም አገልግሎት ተገርመው ሲያወሩ አሊያም ሲጽፉ ሊሰሙ ይችላሉ። ይህ ግን ዛሪ ኒውዮርክን ለረገጠ የዓለም ሰው ሁሉ ምቹ አገልግሎት የሚሰጠው የምድር ውስጥ የባቡር መንገድ እንዴት እንደታሰበ እና ዘመናትን በብዙ ውጣውረድ ማለፉን የሚያውቁ ጥቂቶች ብቻ ናቸው። አንድ እውነት ግን አለ ዓላሚ፣ ገፈት ቀማሽ እና ፈጻሚ ትውልድ የሌለው ሀገር ቀጣይነቱ ጥያቄ ውስጥ መውደቁ አያጠያይቅም።