Search

10ኛው የከተሞች ፎረም በሰመራ ስታዲየም በተለያዩ ኹነቶች እየተከበረ ይገኛል

ቅዳሜ ኅዳር 06, 2018 120

“የከተሞች ዕድገት ለኢትዮጵያ ልህቀት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ በሚገኘው 10ኛው የከተሞች ፎረም ላይ ከ150 በላይ ከተሞችና ከተለያዩ ተቋማት የመጡ እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛል።
ከደቂቃዎች በኋላ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒን ጨምሮ የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የመክፈቻው ስነ-ስርዓት ይከናወናል ተብሎ ይጠበቃል።
ክብረ በዓሉ በተለያዩ ኹነቶች ለቀጣዮቹ አምስት ቀናት ይከበራል።
 
በሁሴን መሀመድ