የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ለ5ሺህ ሰዎች ነጻ የሕክምና አገልግሎት በቦሌ ክፍለከተማ መሰጠት ጀመረ።
በመሰጠት ላይ የሚገኘው የቅድመ ምርመራ እና ሕክምና አገልግሎት፤ የክረምት በጎፍቃድ አገልግሎት አካል ነው።
የቦሌ ክፍለከተማ አስተዳደር ከሌሎች የግልና የመንግስት የጤና ተቋማት ጋር በመተባበር በክረምት በጎ ፈቃድ መርሐ ግብር፤ ከ13ሺህ 500 በላይ ለሆኑ የክፍለከተማው ነዋሪዎች ነጻ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ማቀዱን አስታውቋል።
የህጻናትና አዋቂዎች ቅድመ ምርመራ አገልግሎትንና ሕክምናን የመስጠት አገልግሎቱ አጠቃላይ ሕክምናን፣ የነርቭ ፣ ከአንገት በላይ ፣ የማህጸን በርና የጡት ካንሰር እንዲሁም ስኳርን ጨምሮ የተለያዩ ነጻ ሕክምናዎች ይሰጣሉ።
በሆስፒታል ደረጃ መታየት የሚገባቸው ሕክምናዎችም ጥቁር አንበሳን ጨምሮ በሌሎች ሆስፒታሎች እንዲታዩ ሪፈር ይደረጋል ተብሏል።
በሳራ ሣሕለሥላሴ