Search

ኢትዮጵያ የተወሰዱባትን 12 ውድ ቅርሶች ተረከበች

ረቡዕ ኅዳር 10, 2018 224

በ1920ዎቹ ከኢትዮጵያ የተወሰዱ 12 ውድ ቅርሶችን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር ተቋም ተቀብሏል::
ቅርሶቹን የፕሮፌሰር ራሞን አያት እንዲሁም በ1920ዎቹ በኢትዮጵያ የጀርመን ልዑክ በነበሩት ፍራንዝ ዊስ የአገልግሎት ዘመን ከኢትዮጵያ የተወሰዱ ሲሆን፣ ፍራንዝ እና ባለቤታቸው ሄድዊግ ገንዘብ ከፍለው የሰበሰቧቸው ናቸው፡፡
ለዩኒቨርሲቲው ከተበረከቱት ውድ ቅርሶች ውስጥ ዘውድ፣ ጋሻ፣ ጎራዴ፣ ዝናር፣ ስዕሎች እንዲሁም ከራስ ተፈሪ መኮንን የተበረከቱ ስጦታዎች ይገኙባቸዋል፡፡
 
የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ፤ ቅርሶቹ የኢትዮጵያ ሃብቶች ከመሆናቸው በተጨማሪ ለጥናት እና ምርምር በግብዓትነት የሚያገለግሉ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
በመላው ዓለም በግለሰቦች እጅ እና በተቋማት ውስጥ የሚገኙና የኢትዮጵያ ታሪክ አስረጂ የሆኑ ጥንታዊ ቅርሶች ወደ ሃገር እንዲመለሱ የማድረጉ ጥረትም ይቀጥላል ሲሉም አስታውቀዋል።