Search

ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ ገቡ

ሓሙስ መጋቢት 17, 2018 88

የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ 11ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ማላቦ ኢኳቶሪያል ጊኒ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ማላቡ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢኳቶሪያል ጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ማኑዌል  ኡሳ ኡዙዌን ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የአፍሪካ፣ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት 5 አስርት አመታት በፊት .. 1975 በቶጎ በተካሄደው ሎሜ ኮንቬንሽን ነበር የተጠነሰሰው፡፡

በሰኔ ወር በዚያው ዓመት ደግሞ ከአፍሪካ፣ካርቢያን እና ፓሲፊክ የተወጣጡ 46 ሀገራት በፈረሙት የጆርጅታውን ስምምነት መሰረት ድርጅቱ ተመስርቷል።

በተለያዩ የታሪክ ምዕራፎች ያለፈው ድርጅቱ አሁን ላይ 79 ሀገራትን በአባልነት ማካተት የቻለ ሲሆን የተፅዕኖ ደረጃውም በዚያው ልክ እያደገ ነው የመጣው።

ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት ከንግድ እና ኢኮኖሚ ትብብር በተጨማሪ የልማት ፣ዴፕሎማሲ፣ ፖለቲካዊ እና አለም አቀፍ የፍትህ ጉዳዮች የሚንሸራሸሩበት መድረክ እየሆነ መጥቷል።

11ኛው የአፍሪካ፣ካሪቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ከመጋቢት 18- 20 / 2018 ድረስ የሚቆይ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

በጉባኤው ከሶስቱም ክልሎች የሚገኙ የሀገራት መሪዎች እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች  እንደሚገኙ ይጠበቃል።

#EBC #Ethiopia #Africa #PresidentTayeAtskeSelassie #EquatorialGuinea #Malabo #OACPS #Diplomacy