ትላንት የተጀመረው የቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ የአየር ንብረት ቀውሱን እና ሌሎች ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶችን የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እንዲሠራ አሳሰበ።
ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ምድር ጆሃንስበርግ ላይ የተካሄደው የቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ በማሳለፍ ተጠናቅቋል፡፡
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል አቀባይ ቪንሰንት ማግዌንያ፤ የጉባኤው አጀንዳዎች ወደኋላ እንደማይመለሱ እና በትኩረት ተግባራዊ እንደሚደረጉ ገልጸዋል።
ቃል አቀባዩ ቪንሰንት ማግዌንያ አክለውም፣ "አጀንዳዎቹ ሁሉን ያማከሉ፣ አሳታፊ እና ወደ ተግባር የሚቀየሩ እንዲሆኑ ከዓመት በላይ ተደክሟል፤ ያለፈው ሳምንት ደግሞ ለቅመደ ዝግጅቱ ልዩ ትኩረት አድርገን ሠርተናል" ብለዋል።
ጉባኤው የመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮችን ያየበት መንገድ አላሳመነኝም የምትለው አርጀንቲና አጀንዳው ላይ ጥርጣሬ እንዳላት ጠቅሳ፣ ለስብስቡ መንፈስ ግን እንደምትተባበር አስታውቃለች፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ምድር የተካሄደውና ኢትዮጵያ ተጋባዥ ሆና የቀረበችበት የቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እያከናወነች ያለውን ሥራ ለጉባኤው አቅርባለች፡፡
በዚህ ረገድም ኢትዮጵያ እየተከተለችው ባለው መንገድ ዓለም ለአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ መፍትሔ እንዲያበጅ ጥሪ አስተላልፋለች፡፡
በለሚ ታደሰ
#Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia #G20Summit