የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በ7ኛው የአፍሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት የመሪዎች እና የመንግሥታት ኃላፊዎች ጉባዔ ለመካፈል ሉዋንዳ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንት ታየ አንጎላ ዋና ከተማ ሉዋንዳ ሲደርሱ ደማቅ አቀባባል ተደርጎላቸዋል።
ፕሬዚዳንቱ በጉባዔው ላይ በሁለቱ አህጉራት የጋራ ትብብር እና ብልጽግና ዙሪያ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህም በኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በምታከናውናቸው የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች እንዲሁም በኢኮኖሚ እና በቴክኖሎጂ ለውጥ ለማምጣት በምታደርገው የዲጂታል ሽግግር ስኬታማ ጥረት ዙሪያ ገለጻ ያደርጋሉ።
ከዋናው ጉባዔ ጎን ለጎንም፥ በሰላም እና ደኅንነት እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የሚደረጉ የሁለትዮሽ ትብብሮችን የማጠናከር ዓላማ ያላቸው ምክክሮችን ያደርጋሉ።
ለ2 ቀናት በሉዋንዳ የሚካሄደው 7ኛው የአፍሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት የመሪዎች እና የመንግሥታት ኃላፊዎች ጉባዔ በንግድ፣ በዘላቂ ልማት፣ በአረንጓዴ ልማት እና በዲጂታል ሽግግር ዙሪያ ሰፋ ያለ ምክክር እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
በሙሐመድ አልቃድር
#ebcdotstream #7thAUEUSummit #Angola #Luanda