የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በተቀበሉበት ወቅት፣ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እና ፓርክን በጋራ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ፤ ለጥቁር ሕዝቦች ነፃነት ትግል ውድ ዋጋ ለከፈሉ ጀግኖች መታሰቢያ በተገነባው ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ አክለውም፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ እና በውቧ መዲና አዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ፣ ጊዜያቸው ፍሬያማ እንዲሆን በራሳቸውና በከተማ አስተዳደሩ ስም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
