Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሲንጋፖር አቻቸው ጋር በአዲስ አበባ

ሰኞ ኅዳር 15, 2018 155

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ይፋዊ የአቀባበል ሥነሥርዓት አካሂደዋል።
የአቀባበል ሥነሥርዓቱ ወዳጅነትን የሚያመላክት የዛፍ መትከል መርሃግብር፣ የብሔራዊ ሙዚየም ታሪካዊ ቁሶች እና ምድረግቢ ጉብኝት፣ የሁለትዮሽ ውይይቶች ብሎም በክሂሎት ልማት እና የካርበን ብድር የመግባቢያ ስምምነቶች ፊርማን አስቀድሞ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫን ያካተተ ነበር።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዋንግ ጉብኝት በሰኔ 2017 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሲንጋፖር ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የተካሄደ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መካከል እያደገ የመጣውን ግንኙነት የሚያሳይም ነው።
ሁለቱም መሪዎች በጉብኝቱ የኢኮኖሚ ትብብርን ለማላቅ፣ ተቋማዊ መስተጋብርን ለማጠናክር ብሎም የወል ቅድሚያዎቻቸውን ከፍ አድርጎ ለመከወን መንገዶችን ተመልክተውበታል።