Search

የአየር ንብረት ለውጥ እየፈተናቸው ያሉት ሆንግ ኮንግ እና ደቡብ ቻይና

ከወደእሲያ በሆንግ ኮንግ እና በደቡብ ቻይና ከተሞች የአየር ንብረት መዛባት ጉዳት እያስከተለ ነው። 

በሆንግ ኮንግ እና በደቡብ ቻይና የፐርል ወንዝ ዴልታ ዙሪያ በሚገኙ ከተሞች የአየር ሁኔታ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

በአካባቢዎቹ በተከሰተው ከባድ አውሎ ንፋስ የቀላቀለ ጎርፍ ምክንያት ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች እና የተለያዩ ተቋማት ተዘግተዋል።

 

 

 

በሆንግ ኮንግ ከሚገኘው ትልቁ ሆስፒታል ከባድ ጎርፍ በመከሰቱ የጤና ዘርፉ ባለስልጣናት ክሊኒኮች እንደሚዘጉ ተናግረዋል።

በቻይና ግዛቶች የተከሰተው ከባድ የጎርፍ መጥለቅለቅ እና የአውሎ ንፋስ አደጋ አስጊ እንደሆነ የሜቲዎሮሎጂ ባለሙያዎችን ጠቅሶ የዘገበው ሬውተርስ ነው።

አደጋው ሰዎችን እስከ ሞት የሚያደርስ፣ ሺዎችን የሚያፈናቅል እንዲሁም በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር የኢኮኖሚ ኪሳራ ሊያደርስ እንደሚችልም ተሰግቷል።

 

በሄለን ተስፋዬ