Search

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት ሆነው ተመረጡ

ረቡዕ ኅዳር 17, 2018 104

በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ኮንቬንሽን መሠረት የኢትዮጵያ የኮፕ 32 አስተናጋጅ ሀገር መሆኗን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት አድርጎ ሰይሟል።

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሀገር ውስጥ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከተባበሩት መንግሥታት አካላት እና አለምአቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር የኮፕ 32 ዝግጅትን የሚመሩ ይሆናል።  

የኢትዮጵያ መንግሥት የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ኮንቬንሽን አባል ሀገራት ለኢትዮጵያ የማዘጋጀት ኃላፊነት በመስጠታቸው ምስጋናውን አቅርቦ፤ በዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ አስተባባሪነት ከዓለም የአየር ንብረት ጥበቃ ማኅበረሰብ ጋር በቅርበት ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።