ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኮፕ 32ን በውጤታማነት ለማሠናዳት የሚያስችል አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮፕ 32 ቁልፍ የዝግጅት ተግባራትን ለማቀናጀት ከሚያስችለው የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ውይይት አድርገዋል።
ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ለማስተናገድ ያላትን ቁርጠኝነት በሚያመላክተው በዚህ ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውጤታማ ጉባኤን ለማሠናዳት የሚያስችሉ ሀሳቦች ላይ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ኮፕ 32 ጉባኤን ለሀገር ግንባታ እና ለገጽታ ግንባታ መጠቀም አለብን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝም አቅም ለዓለም ለማሳየት የሚረዳ ትልቁ ጉባኤ ይሆናል ሲሉም አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ስኬታማነት በትኩረት እንደምትሠራም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በድጋሚ አረጋግጠዋል።