ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ስደተኞች ተቀብላ የምታስናግድ ሀገር መሆኗን መረጃዎች ያመላክታሉ።
የውጭ ሀገር ዜጎች በተለየያ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ከገቡ በኋላ ሥራ እየሰሩ ኑሯቸውን ሲመሰርቱ ይታያል።
ሶሪያዊው አህመድ ሙስጠፋ በስደት ወደኢትዮጵያ መምጣቱን ይናገራል።
በአዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ በከፈተው ምግብ ቤት የተለያዩ የሶሪያ ምግቦችን በማዘጋጀት ኑሮውን ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ለ6 ዓመታት እንደቆየ የሚናገረው ስደተኛው በቆይታው ከኢትዮጵያዊት እንስት ጋር ትዳር መስርቶ እየኖረም መሆኑን ተናግሯል።
ተቀጥሮ ከሚሰራበት ቤት የሚያገኘውን ገንዘብ በመቆጠብ የራሱን ምግን ቤት እንደከፈተም ይናገራል፡፡
የሚሰራቸው ምግቦች የሶሪያ ምግቦች ሲሆን በአካባቢው ማህበረሰብ ተወዳጅነትም አትርፏል።
“ለአዲስ አበባ ሕዝብ ከፍተኛ ምስጋናም አለኝ” ይላል አህመድ።
ኢትዮጵያ እንደ ራሷ ዜጋ አድርጋ ተቀብላ ለዚህ አብቅታኛለች ሲልም ተናግሯል፡፡
በሜሮን ንብረት