Search

ቻይና አዲስ ሳተላይት በተሳካ ሁኔታ ወደ ህዋ አመጠቀች

ማክሰኞ ኅዳር 23, 2018 130

ቻይና አዲስ ሳተላይት ወደ ህዋ ያመጠቀች ሲሆን ሳተላይቷ ወደ ታቀደው ምህዋር በተሳካ ሁኔታ መድረሷ ተነግሯል።
ሺጂያን-28 ሳተላይት የጠፈር አካባቢን ለመከታተል ጥቅም ላይ እንደምትውል ተዘግቧል።
ሳተላይቷ በተሻሻለው የሎንግ ማርች-7 ተሸካሚ ሮኬት እሁድ ዕለት እንድትወነጨፍ መደረጉም ተገልጿል።
የቻይናው "ሎንግ ማርች" ሮኬት 611ኛውን ተልዕኮውን ነው በተሳካ ሁኔታ ያከናወነው።
ቀደም ሲል እ አ አ ኅዳር 19 ቻይና ተዛማጅ ለጠፈር አካባቢ ጥናቶች እና ለቴክኖሎጂ ሙከራዎች ሦስት ሳተላይቶችን ሺጂያን-30A፣ 30B እና 30C ማምጠቋ ይታወሳል።
በሴራን ታደሰ