Search

በጋዛ 54 ጥንዶች በአንድ ቀን ጋብቻቸውን ፈጸሙ

ረቡዕ ኅዳር 24, 2018 224

በደቡብ ጋዛ በእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት በእጅጉ በተጎዳችው ካን ዩኒስ መንደር ውስጥ 54 ጥንዶች በአንድ ቀን ጋብቻቸውን ፈጽመዋል።

በእስራኤል እና ሀማስ መካከል በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት የጋዛ ሰርጥ ወደ ሰላም እየተመለሰ በሚገኝበት በዚህ ወቅት የተደረገው የሰርግ ስነ ስርዓት በብዙዎች ዘንድ የተስፋ ነፀብራቅ ተደርጎ ተወስዷል።

እንደዚህ አይነት የደስታ ጊዜ ያስፈልገን ነበር፤ ከነበርንባቸው አስከፊ ጊዜያቶች በኋላ በደስታ ተሰባስበናል፤ ይህ ጌዜ የማይታመን ነው ሲሉ ተጋቢ ሙሽሮቹ ተናግረዋል።

ከጦርነቱ በኋላ አዲስ ህይወት ለመጀመር ጉዞ ላይ ነን፤ ሰላም መሰረታዊ ነገር ነው፤ ከዚህ በኋላ ወደ ጦርነቱ እንደማንመለስ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።

የጋብቻ ስነ ስርዓቱ የተዘጋጀው በኤሚሬትሱ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አል-ፋሪስ አል-ሻሂም ፋውንዴሽን ሲሆን የጋብቻ ስፍራውን በፈራረሱ የጋዛ መንደሮች ያደረግነው የጋዛን ተስፋ የነገን ተስፋ ለማሳየት ነው ሲሉ የድርጅቱ የሚድያ ሀላፊ ሻሪፍ አል-ነይብ ለ ፍራንስ 24 ገልጸዋል።

ጥቅምት 10 በእስራኤል እና ሀማስ መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የጋዛ ነዋሪዎች ቀስ በቀስ ወደ መደበኛ ህይወታቸው እየተመለሱ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ

#ebcdotstream #Gaza #wedding