Search

ትናንትን ከነገ ለማስተሳሰር፣ የዛሬን ድልድይ በመገንባት የታሪክ ዐሻራ ማኖር ያስፈልጋል

ዓርብ ኅዳር 26, 2018 128

ትናንትን ከነገ ለማስተሳሰር የዛሬን ድልድይ በመገንባት የታሪክ ዐሻራ ማኖር አስፈላጊ ነው ሲሉ የታሪክ ተመራማሪው ታምራት ኃይሌ (ዶ/ር) ገለጹ።

ዶ/ር ታምራት ከኢቲቪ 57 ዜና ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ የመደመር መንግሥት በኢትዮጵያ ትናንት፣ ዛሬ እና ነገ መካከል ጥልቅ ትስስር ያለው እሳቤን የሚከተል ነው ብለዋል።

የመደመር መንግሥት ታሪክን እንደ ሂደት እደሚመለከት ጠቅሰው፤ ትናንትን ከነገ ለማስተሳሰር፣ የዛሬን ድልድይ በመገንባት የታሪክ ዐሻራ ማኖር እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።

ከትናንት መልካሙን በመውሰድ፣ መልካም ካልሆነው ደግሞ ተምሮ እንዳይደገም መሥራት የመደመር መንግሥት መገለጫ መሆኑን አክለዋል።

ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ይበልጥ ለማጎልበት፣ ከፋፋይ ትርክትን ወደ ጎን በመተው አሰባሳቢ ትርክት መገንባት እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ ይህም ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት የነበሯትን መልካም አጋጣሚዎች ሳትጠቀም በመቅረቷ ረጅም ጊዜ መፍጀቷን ያነሱት ተመራማሪው፤ የመደመር መንግሥት የወል ትርክት በመፍጠር ይህን የታሪክ ስብራታችንን ለመጠገን የጀመረው እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ገልጸዋል።

በሜሮን ንብረት

#ኢቲቪ #ኢትዮጵያ #መደመር #የመደመርመንግሥት #ሀገረመንግሥት