ባሕር ዳር እና የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት እያስመረቁ ነው።
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ሲያሰለጥናቸው የቆዩ 6 ሺህ 492 ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።
ከተመራቂዎች መካከል 1 ሺህ 691 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በሌላ በኩል የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 45 ተማሪዎች እያስመረቀ እንደሚገኝ አሚኮ ዘግቧል።