Search

ከጎሮ መታጠፊያ እስከ ኮዬ ፈጬ አደባባይ ድረስ ያለውን የ10.5 ኪሎ ሜትር አዲስ የኮሪደር ልማት ስራ መጀመሩን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አበሰሩ

ሓሙስ ሰኔ 11, 2018 45

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከጎሮ መታጠፊያ እስከ ኮዬ ፈጬ አደባባይ ድረስ ያለውን አዲስ የኮሪደር ልማት ስራን በተቀናጀና በተደራጀ አግባብ መጀመሩን አብስረዋል።

May be an image of one or more people, car and road

ከጎሮ መታጠፊያ - ኮዬ ፈጬ አደባባይ ያስጀመርነው የኮሪደር ልማት አጠቃላይ የመንገዱ ርዝመት 10.5 ኪሎ ሜትር ሲሆን፣ የመንገዱ ስፋት 70 ሜትር  (ስምንት ሌን ያለው) ከነግሪነሪው 124 ሜትር፣ 21 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የሳይክል መንገድ፣ 21 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና  በሁለቱም በኩል 4.5 ሜትር ስፋት ያለው  የእግረኛ  መንገድ፣ ሰፊ የአረንጓዴ ሽፋን እንዲሁም የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያም ይኖረዋል።

ኮሪደር ልማቱ በከተማችን ቀደም ሲል የለሙ መሰረተ ልማቶችን በከፍተኛ ሁኔታ  የሚያስተሳስር፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን የሚያነቃቃ፣ በመንገዱ ላይ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ የሚፈታ ይሆናል ያሉት ከንቲባዋ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ጋር የተገናኘ በመሆኑም ሀገራዊ ሁነቶችን ለማስተናገድ አመቺ ሁኔታን የሚፈጥር፣ እንዲሁም የአካባቢውን ስታንዳርድ በእጅጉ በሚያሳድግ ሁኔታ የሚሰራ ነው ብለዋል።

May be an image of one or more people

ከንቲባ አዳነች በኮሪደሩ ሞሎች፣ የቢዝነስ ተቋማት እና ሌሎች ኮሚኒቲዎች የሚገነቡ ሲሆን  ከዚህ ቀደም በመንገዱ ዙሪያ ከደረጃ በታች ይሰጡ የነበሩ አገልግሎቶችን ከፍ ባለ ደረጃ ለመስጠት በሚያስችል መልኩ በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትልቅ ርብርብ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

ይህ ኮሪደር ከከተማችን እልፎ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው፣ ለአካባቢው ነዋሪ ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር፣ አካባቢውን ወደ ትልቅ የንግድ እንቅስቃሴ የሚቀይር ነው ያሉት ከንቲባዋ ለአካባቢው ነዋሪዎችም ትብብራችሁ እንደ ወትሮው የተጠናከረ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

አንቲባዋ አክለውም በስራው ውስጥ የምትሳተፉ ኮንትራክተሮች፣ ማህበራት፣ አማካሪዎች በአጠቃላይ ባለድርሻ አካላት በትብብር በፍጥነት በጋራ እንድናሳካው ጥሪዬን አቀርባለሁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።