Search

አካል ጉዳተኝነት የዓለም ዋንጫን ከመታደም ያላገደው የእግር ኳስ ወዳጅ

ሓሙስ ሰኔ 11, 2018 42

ለአብዛኞቹ ደጋፊዎች እግር ኳስ የሚታይ ነገር ነው። መስማት የተሳነው ሆኖ የተወለደውና ቆይቶም ለዓይነ ስውርነት የተዳረገው ሎኤራ፤ በሜክሲኮ እና በደቡብ አፍሪካ መካከል የተደረገውን የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ በንዝረት እና ውስጥ በነበሩ የንክኪ የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚዎች አማካኝነት ተከታትሏል።

የፊፋ 2026 ዓለም ዋንጫ አካል የሆነው ይህ እቅድ፣ መስማትና ማየት የተሳናቸው ደጋፊዎች የጨዋታውን እያንዳንዱን ቅጽበት እንዲከታተሉ ያስቻለ ሲሆን፤ ይህም በዓለም ትልቁ የስፖርት መድረክ በሁሉም ሰው ዘንድ ደስታን መፍጠር እንደሚቻል ያረጋገጠ ነበር።

“ይህ ሁኔታ ለእኔ እጅግ በጣም አስደሳች ሆኖ አግኝቼዋለሁ" ሲል የዓለም ዋንጫ ጨዋታን በንዝረት እና በንክኪ የምልክት ቋንቋ ትርጉም ለመጀመሪያ ጊዜ የታደመው ሆሴ ዴ ሄሱስ ሎኤራ ስሜቱን አካፍሏል ሲል ሚሌኒዮ ኢንፎርሜሽን ዘግቧል።