ላለፉት 15 ዓመታት ተዘግቶ የቆየው የዓለማችን ትልቁ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ፉኩሺማ ዳግም ወደ ሥራ ሊገባ መሆኑ ተሰምቷል።
እ.አ.አ በ2011 በጃፓን የተከሰተው እና በሬክተር ስኬል 9 የተለካው ከባድ ርዕደ መሬት ለበርካታ ጃፓናውያን ሕልፈት ምክንያት የሆነ ነበር።
በተጨማሪም ርዕደ መሬቱ ያስከተለው ሱናሚ (የውቅያኖስ ውሃን የያዘ ከባድ አውሎ ነፋስ) በግዙፉ የሀገሪቱ ኒውክሊየር ጣቢያ፣ ፉኩሺማ ላይ ከባድ ጉዳት አስከትሏል።
በጉዳቱ የኒውክሊየር ጣቢያው የተወሰነ ክፍል ከቁጥጥር ውጪ በመውጣቱ ከፍተኛ ጨረር ከጣቢያው አፈትልኮ ጉዳት አስከትሏል።
በዚህም በወቅቱ ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚደርሰውን የጃፓን የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ ይሸፍን የነበረው ፉኩሺማ የኒውክሊየር ኃይል ጣቢያ እስከአሁን ድረስ ዝግ ሆኖ ቆይቷል።
በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ጃፓን የኤሌክትሪክ ፍጆታዋን ለመሸፈን በዓመት ከ68 ቢሊዮን ዶላር በላይ እያወጣች የተፈጥሮ ጋዝ እና የድንጋይ ከሰል ወደ ሀገር እያስገባች ትገኛለች።
ይህ ደግሞ በኢኮኖሚው ላይ ትልቅ ጫና እያሳደረ በመምጣቱ ሀገሪቱ ትልቁን የኃይል ማመንጫዋን ፉኩሺማን ዳግም ለመጠቀም እንደተገደደች የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል።
ጃፓን በአካባቢ ሥነ ምህዳር መዛባት እና በአየር ብክለት ስጋት ፉኩሺማን ጨምሮ 54 የኒውክሊየር ጣቢያዎቿን ዘግታ የቆየች ሲሆን፤ አሁን ላይ አንዳንዶቹን ቀስ በቀስ ሥራ እያስጀመረች ትገኛለች።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
#EBC #ebcdotstream #Japan #NuclearEnergy #Fukushima