Search

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ከዓለም ጋር እኩል መራመድ

ሰኞ ታኅሣሥ 13, 2018 30

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ተጠናቅቆ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ይፋ ተደርጓል።

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ዋና ዓላማው አገልግሎትን ማስፋት፣ ለሁሉም ዜጋ እኩል ዕድል መፍጠር እና በዜጎች እና በተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ነው።

በባንኮች መካከል ትሥሥር እንዲፈጠር የሚሠራው የኢት ስዊች ዋና የፖርትፎሊዮ ኦፊሰር አቤኔዘር ወንደወሰን ከኢቲቪ አዲስ ቀን መሰናዶ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የባንኮችን አሠራር እንደሚያዘምን ተናግረዋል።

የሳይበር ደኅንነት የብሔራዊ ጥቅም እና የሉዓላዊነት ጉዳይ መሆኑን የጠቀሱት ኦፊሰሩ፣ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

ዛሬ ላይ ከአንዱ ባንክ ወደ ሌላኛው ባንክ በትሪሊዮን የሚገመት ገንዘብ እንደሚዘዋወር በመጠቆም፣ ይህም የኅብረተሰቡ የባንክ አጠቃቀም ወደ ዲጂታል እየተቀየረ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።

በዚህ የዲጂታላይዜሽን ዘመን ኤአይን (AI) በመጠቀም ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተሠሩ ነው፤ ባንኮችም ይህን አሠራር በመጠቀም አገልግሎታቸውን እያሳለጡ ይገኛሉ።

አሁን ላይ ኢትዮጵያ የጀመረችው የዲጂታል ጉዞ ከመላው ዓለም ጋር እኩል እንድትራመድ እንደሚያደርጋትም የኢት ስዊች ዋና የፖርትፎሊዮ ኦፊሰር አቤኔዘር ወንድወሰን ተናግረዋል።

በሜሮን ንብረት

#Ebc #ebcdotstream #DigtalEthiopia2030