Search

ቱሪዝሙ የፈጠረው የኢኮኖሚ አቅም

ዓርብ ታኅሣሥ 24, 2018 40

አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ ከመሄድ የተሻገረ ብዝኃ የኢኮኖሚ ምሕዳር የፈጠረው የመደመር መንግሥት ቱሪዝምን አንዱ የኢኮኖሚ ዕድገት ምሰሶ አድርጎታል::

ይህም በመሆኑ የተረሱ እና አገልግሎት የማይሰጡ የነበሩ መዳረሻዎችን ወደ ምቹ እና ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻ መቀየር ተችሏል፡፡

ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ የቱሪዝም መስህቦችን በማልማት ዘርፉ እንዲነቃቃ አስችሏል፡፡

በዚህ ሀሳብ የሚስማሙት የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስሊሺ ግርማ ለዚህ ሁሉ ለውጥ ቁልፉ የመደመር መንግሥት ነው ይላሉ::

አቶ ስሊሺ ግርማ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የመደመር መንግሥት ከቢሮ እስከ ሀገር በሚል እሳቤ በኢትዮጵያ በየትኛውም አካባቢ የተፈጥሮ ጸጋ እንዳለ ሰርቶ ማሳየት እንደቻለ ነው የጠቆሙት፡፡

በገበታ ለሀገር፣ ገበታ ለሸገር እና ገበታ ለትውልድ የሚሰሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ለሀገር ኢኮኖሚ ምሶሶ እየሆኑ መምጣታቸውንም ተናግረዋል፡፡

ይህም በመሆኑ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የቱሪዝም መዳረሻዎች ካርታ ውስጥ መግባት መቻሏን አስታውሰዋል፡፡

በሀገራችን የነበሩ የቱሪዝም መዳረሻዎች ለረጅም ዘመናት ሳንሰራባቸው በመቆየቱ በዘርፉ ማግኘት ያለብንን ሀብት ሳናገኝ ቆይተናል የሚሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ የባከኑ  ጊዜያትን ለማካካስ የመደመር መንግሥት በቁርጠኝነት በዘርፉ ላይ እየሰራ እንደሆነ ነው ያነሱት፡፡

ኢትዮጵያ ለኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን ቱሪዝም ተመራጭ እየሆነች ስለመምጣቷ አንስተው፤ በ2017 በጀት ዓመት ከ150 በላይ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን ማስተናገድ ስለመቻሉ ገልፀዋል፡፡

በተለይም በአዲስ አበባ የመሰረተ ልማት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች መሟላት ከተማዋን ለኮንፍረንስ ቱሪዝም ተመራጭ እንዳደረጋት አንስተዋል።

በሀገሪቱ በተሰሩ የቱሪዝም መዳረሻዎች ከ2 ሚሊዮን የሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር መቻሉንም ነው የጠቀሱት፡፡

በዘርፉ በባለፈው ዓመት በውጭ ምንዛሬ ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

በሜሮን ንብረት

#Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia #Tourism