በኢትዮጵያ ደብረሲና አካባቢ በሬክተር ስኬል 4.6 ማግኒቲዩድ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ማዕከል አስታውቋል።
ዓርብ ነሐሴ 02/2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 7:18 ሰዓት የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አቦምሳ፣ አዋሽ፣ ቆቦ እና ሮቢት አካባቢዎች ላይ መሰማቱን ነው መረጃው ያመለከተው።
በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎችም ንዝረቱ እንደተሰማቸው ነዋሪዎች በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው እየገለጹ ይገኛሉ።
#EBC #ebcdotstream #earthquake