የአዲስ አበባ የኮሪደር እና የወንዝ ዳር ልማቶች ለመዲናችን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈቱ፣ ደረጃውን የጠበቀ የክትመት ንጋት እና የማንሰራራት ዘመን አብሳሪዎች ናቸው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ደረጃቸውን የጠበቁ ከተሞች የሀገራት ስልጣኔ፣ የተፈጥሮ ሚዛን ጥበቃ፣ የሕዝቦች የእሳቤ ከፍታ አድማስ እና አጠቃላይ የልማት እንቅስቃሴዎች የሚነበብባቸው ገጾች ናቸው ብለዋል።
አዲስ አበባ በልጆቿ ብርቱ ክንዶች እየለማችና እየደመቀች፣ በነዋሪዎቿ ትጋት እየፈካች እና እየተዋበች በተግባር ስሟን እየሆነች ያለች ከተማ ናት ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት ፅሑፍ።
የሀገራችንና የአፍሪካ መዲናችን የውበት ብቻ ሳይሆን የቀልጣፋ አገልግሎት፣ የመዝናኛ ብቻ ሳይሆን የምቹ ኑሮ፣ ከዚህም ባለፈ አጠቃላይ የሀገራችን ፈጣን ልማት የሚቃኝባት የዕድገታችን ማሳያ ናት ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።