Search

የሸበሌ ሪዞርት በዛሬው ዕለት በይፋ ተመረቀ

ቅዳሜ ጥር 23, 2018 265

የሸበሌ ሪዞርት በዛሬው ዕለት በይፋ መመረቁን የጠቅላይ ሚኒስትር /ቤት አስታወቀ።

ሪዞርቱ የገበታ ለትውልድ ዋነኛ ፕሮጀክት ሲሆን 385 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው፡፡

በአንድ ጊዜ እስከ 400 እንግዶችን ማስተናገድ የሚችሉ ሦስት ምግብ ቤቶች፣ ልዩ የባሕል ማዕከል፣ ዘመናዊ የክብረ-በዓላትና የስብሰባ አዳራሾች፣ የሕፃናት መጫወቻ ስፍራዎችና 15.4 ኪሎ ሜትር የሚረዝሙ የእግረኛ መንገዶችን የያዘው የሸበሌ ሪዞርት፤ ማኅበራዊ ትስስርን ለማጠናከር ታሳቢ ተደርጎ የተገነባ ነው።

10 ሺህ የፍራፍሬ ተክሎች ካረፉበት የፍራፍሬ ፓርክ ጀምሮ እስከ ዋናው የግመል ፓርክ ድረስ፤ እያንዳንዱ የሪዞርቱ ገጽታ የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊና ባህላዊ ሐብት የሚያንፀባርቅ ነው።

51 የተጠናቀቁ የመኝታ ክፍሎችና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚገኙ የቱሪዝም አገልግሎቶች እውን የሆነው ሸበሌ ሪዞርት፤ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በሚደረገው ጉዞ ውስጥ ትልቅ ታሪካዊ እጥፋት ነው።

ይህ ፕሮጀክት ህልምን ወደ እውነት የመለወጥ፤ የኢትዮጵያን የተፈጥሮና የባህል ጸጋዎች መላው ዓለም የሚካፈለው ቅርስ የማድረግ የመደመር መንፈስ በተግባር የታየበት ታላቅ ስራ ነው፡፡

#EthiopianBroadcastingCorporation #EBC #ebcdotstream #Ethiopia #Shebeleresort