የሸበሌ ሪዞርት ኢትዮጵያ የምታልም ብቻ ሳትሆን ሕልሟን ወደ እውነት የምትቀይር እና የምትኖር ሀገር መሆኗን በተግባር አሳይቷል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፣ ከ’ገበታ ለትውልድ’ ዐቢይ ፕሮጀክቶች መካከል ሁለተኛውን እና በ385 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውን የሸበሌ ሪዞርትን መርቀው ለአገልግሎት ማብቃታቸውን አስታውቀዋል።
ይህ ሪዞርት መዝናኛ ስፍራ ብቻ ሳይሆን፤ የዘመናዊ ሥነ-ሕንጻ ጥበብን ከሶማሌ ክልል ባሕላዊ እሴት ጋር አቀናጅቶ የያዘ የታሪክ ማኅደር እንደሆነ ነው የገለጹት።
ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የገባነውን ቃል በተግባር ያረጋገጠ የምስራቁ የሀገራችን ክፍል ትልቅ ሥራ እንደሆነም አመላክተዋል።
በክልሉ የሚገኘው እጅግ ሰፊ እና ማራኪ ተፈጥሯዊ ጸጋ በመደመር ዕሴትና ትብብር ወደ ልማት ሲለወጥ፤ ኢትዮጵያ የምታልም ብቻ ሳትሆን ህልሟን ወደ እውነት የምትቀይር እና የምትኖር ሀገር መሆኗን በተግባር አሳይቷል።
#EthiopianBroadcastingCorporation #EBC #ebcdotstream #Ethiopia #Shebeleresort