Search

ፀጋን ወደ ሀብት፣ ታሪክን ወደ ብልፅግና - የኢትዮጵያ መነሣት መታያዎች!

ቅዳሜ ጥር 23, 2018 259

ኢትዮጵያ ዛሬ የውበት ብቻ ሳይሆን የሥራ፣ የተስፋ ብቻ ሳይሆን የተጨባጭ ውጤት ምድር እየሆነች ነው።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/)  ከሀሳብ ዘር እስከ ውጤት በሚመነዘር የቃል ጉልበት የተጀመሩት ገበታፕሮጀክቶች፣ ሀገራችን ለዘመናት የኖረባትንየቀለም የዕይታ፣ የመግለጥ ድህነትሰብረው፣ ድብቅ ፀጋዎቻችንን ለዓለም ገበያ እያወጡ ይገኛሉ።

 ገበታ ለሀገርእስከገበታ ለትውልድ የጉዞው ስኬት

የመጀመሪያው ምዕራፍ በነበረውገበታ ለሸገር  የተጀመረው  መዲናዋን የመቀየር ተምሳሌታዊ ጉዞ ፍጥነቱን በመቀየር አድማሱን በማስፋትገበታ ለሀገርፕሮጀክቶች እንደ ጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻ ያሉ ታላላቅ መዳረሻዎች የኢትዮጵያን አዲስ ገፅታ መገንባት ጀመሩ።

ይህ ስኬት ተስፋፍቶ ዛሬገበታ ለትውልድበሚል የላቀ ደረጃ ላይ ደርሷል። እንደ ሃላላ ኬላ፣ ጨበራ ጩርጩራ - የዝሆን ዳና ሎጅ፣ ወንጪ-ደንዲ ኢኮ ሎጅ፦ ጎርጎራ እና ሸበሌ ሪዞርት  የመሳሰሉት  ፕሮጀክቶች ተራ የመዝናኛ ስፍራዎች አይደሉም፤ የኢኮኖሚ ጥንካሬያችን አዳዲስ ምሶሶዎች፣ የመለወጥ አቅማችን ውስጣዊ መገለጫ፣ የመደመር ትውልድ አዲስ ገፅታ ናቸው።

የመደመር እሳቤ 

እነዚህ ሥራዎች በዘፈቀደ የሚከናወኑ ሳይሆኑ በመደመር እሳቤ ተቀድተው የታነጹ ናቸው። መደመር ማለትአቅማችንን ማወቅ፣ ያለንን አቅም ማቀናጀት፣ ለላቀ ውጤትና ከፍታ መነሣትነው። የመደመር መንግሥት፣ የግል ባለሀብቱ እና ሕዝቡ በአንድነት በመቆማቸው፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ የማይታሰቡ የሚመስሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶች እውን ሊሆኑ ችለዋል።

ይህ የእድገት ጉዞ ለዘመናት ኢትዮጵያ በቂ ትኩረት ባልተሰጠው በግብርና ላይ ብቻ የተንጠለጠለውን ኢኮኖሚዋን ወደ ብዝሐ ዘርፍ ኢኮኖሚ  በማሸጋገር (Economic Diversification) ዘላቂ እና የማይናወጥ መሠረት እየጣለች መሆኑን ያሳያል።

የኢትዮጵያ አዲስ ሚና በአፍሪካ

ዛሬ ኢትዮጵያ ለቀጠናው እና ለመላው አፍሪካ የለውጥ ሞተር (Change Agent) እየሆነች ነው። እነዚህ ፕሮጀክቶችአፍሪካውያን በራሳቸው አቅምና እውቀት ታላላቅ ስራዎችን መስራት ይችላሉየሚል ትልቅ ተስፋን ሰጥተዋል። በታላቁ የሕዳሴ ግድብ የጀመርነው የኃይል የበላይነት፣ ገበታ ለትውልድበቱሪዝምና በመሰረተ ልማት እየታጀበ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት እያደረጋት ነው።

ለቀጣይ ትውልድ የሚኖረው ሚና

ለልጆቻችን የምናወርሰው ዕዳን ሳይሆን ሀብትን፣ ውርደትን ሳይሆን ኩራትን ነው።ገበታ ለትውልድማለት ነገ ልጆቻችን በሀገራቸው ተስፋ ቆርጠው እንዳይሰደዱ፣ ይልቁንም በሀገራቸው ፀጋ እንዲጠቀሙና የአለም እንግዶችን በክብር እንዲቀበሉ የሚያስችል የታሪክ አደራ ነው።

ኢትዮጵያ በትጋት ትገነባለች፤ በውበት ትመራለች!

#ebcdotstream #ገበታ_ለትውልድ #መደመር #ኢትዮጵያ #አፍሪካ_ተስፋ #PMAbiyAhmed #TourismEthiopia