ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ የኮመንዌልዝ እና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ይቬት ኩፐር ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።
ከውይይቱ ጎን ለጎን በሁለቱ ሀገራት መካከል የኢንቨስትመንትና የሀብት አስተዳደር የቴክኒክ ትብብርን ጨምሮ ሁለት ግዙፍ የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክቶችን ወደ ተግባር የሚያስገቡ የልማት ስምምነቶች ተፈርመዋል።
ስምምነቶቹም፦ የሁርሶ-አይሻ 400 ኪሎ ቮልት እና የደገሃቡር-ቀብሪደሃር 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክቶች ናቸው።
እነዚህ ስምምነቶች በሀገራቱ መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ በማጠናከር ስትራቴጂካዊ መሠረተ ልማቶችን ለማስፋፋት ትልቅ እርምጃ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።