Search

በሩስያ እና በዩክሬን መካከል የተኩስ አቁም እንዲደረግ ለማግባባት ትራምፕ ከፑቲን ጋር ሊወያዩ ነው

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩስያው አቻቸው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የፊታችን ዓርብ በአላስካ በአካል ተገናኝተው እንደሚወያዩ ገለፁ።

የፕሬዚዳንቶቹ ውይይት ከ3 ዓመት ተኩል በላይ የዘለቀውን የሩስያ ዩክሬን ጦርነት ለማስቆም የሰላም ስምምነት ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

ሩስያ እና ዩክሬን በመካከላቸው ያለውን ጦርነት ለማቆም የተኩስ አቁም ስምምት ለማድረግ ከጫፍ ላይ ደርሰው እንደነበር ያስታወሱት ፕሬዚዳንት ትራምፕ፤ አሁንም የተኩስ አቁም ስምምነቱ እንደሚሳካ ትልቅ ተስፋ እንዳላቸው ገልፀዋል።

ሩስያ እና ዩክሬን በመካከላቸው ያለውን ጦርነት ለማቆም የሚያደርጉት ስምምነት የመሬት ልውውጥን ሊያካትት እንደሚችል የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤትን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ስለጉዳዩ በሰጡት አስተያየት፥ ዩክሬን ለሩስያ አሳልፋ የምትሰጠው አንድም ቁራሽ መሬት የለም ብለዋል።

በላሉ ኢታላ

#EBC #EBCdotstream #Russia_Ukraine #USA_Russia #Trump_Putin